ፍሪድሬሽ ሜርስ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሁነው ተመረጡ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2017ማስታወቂያ
የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በሰጠው ድምፅ ወግ አጥባቂውን የክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ መሪ ፍሪድሪሽ ሜርስን በመራኄ መንግስትነት መርጧል። ሜርስ በመራኄ መንግስትነት የተመረጡት ከምክር ቤቱ አባላት የ325ቱን ድጋፍ አግኝተው ነው። ዛሬ ጠዋት በተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ሜርስ አብላጫ ድምጽ ባለማግኘታቸው ነበር ከሰዓት በኋላ ሁለተኛ ዙር ምርጫ የተካሄደው። በጠዋቱ ምርጫ ሜርስ 310 የድጋፍ ድምጽ ብቻ ነበር ያገኙት። ሜርስ መራኄ መንግሥት ለመሆን ከ630 የጀርመን ምክር ቤት አባላት ቢያንስ የ316ቱን ድምጽ ማግኘት ነበረባቸው። በጀርመን የመራኄ መንግስት ምርጫ ይህን ዓይነቱ ክስተት ሲፈጠር የዛሬው የመጀመሪያው ነው።