ጀርመን፤ ጠንካራ ጥበቃ በቡንደስታግ አካባቢ
እሑድ፣ ጥር 2 2013ማስታወቂያ
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ዋሽንግተን የሚገኘዉን የሃገሪቱን ምክር ቤቶች ሕንፃ አጥር ፈንቅለዉና መስኮት ሰባብረዉ ሕንጻ ዉስጥ ከገቡ በኋላ የምዕራቡ ዓለም ሃገራት ጥንቃቄ እየወሰዱ ነዉ። የጀርመን ፓርላማ ቡንደስታግ የሚገኘዉን የፀጥታ ጥበቃ አባላት ቁጥር መጠናከሩ ተመልክቶአል። ይህ የታወቀዉ የጀርመን ፓርላማ አፈ ጉባኤ ወልፍጋንግ ሾይብለ ዛሬ በጀርመን ዘወትር እሁድ ለሚታተመዉ «ቢልድ አምሶንታግ » ለተሰኘዉ ጋዜጣ ከገለፁ በኋላ ነዉ። ከጥቂት ቀናት በፊት በተሰናበትነዉ የጎርጎረሳዉያኑ 2020 ዓመት የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን ለመግታት ፀድቆ የነበረዉን ጥብቅ የዝዉዉርን ሕግን በመቃወም ጀርመን መዲና በርሊን በጀርመን ፓርላማ አካባቢ በተካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ ፤ ሰልፈኛዉ ፓርላማ አጥሩን ጥሶ ገብቶ ግዙፉ ሕንጻ ደረጃ ላይ ታይቶ እንደነበር የሚታወስ ነዉ።
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ