ጀርመን ኢትዮጵያዉያንን መመለስዋን ቀጥላለች
ማክሰኞ፣ የካቲት 2 2013ማስታወቂያ
ጀርመን ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ወደ ሃገራቸዉ መጠረዝዋን ቀጥላለች። በጀርመን ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና የሰብዓዊ ጉዳይ አቀንቃኞች ይህን የጀርመን መንግሥትን ርምጃ እያወገዙ ነዉ። የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት እጅግ ባየለበት እና ኢትዮጵያ ዉስጥ በትግራይ እና በተለያዩ ክልሎች የተለያዩ ተግዳሮት ባለበት በአሁኑ ወቅት በጀርመን የጥገኝነት ጥያቄ ያቀረቡ ኢትዮጵያዉያን ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ መደረጉ ስህተት ነዉ ሲሉ የሰብዓዊ ጉዳይ አቀንቃኞች ተናግረዋል። በጎርጎረሳዉያኑ 2020 ዓመት ብቻ ከጀርመን 20 ኢትዮጵያዉያን ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ ተደርጎአል።
ዳንኤል ፔልዝ / ይልማ ኃይለሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ