ጀርመን ሕጻናት ስደተኞችን ተቀበለች
ዓርብ፣ ሰኔ 12 2012ማስታወቂያ
ጀርመን በግሪክ የስደተኞች ጣብያ የሚገኙ 243 ሕጻናትና ቤተሰቦቻቸዉን ወደ ሃገርዋ አምጥታ መጠለያ ሰጠች። የጀርመን ሃገር አስተዳደር ሚኒስትር ዜሆፈር እንደተናገሩት ጀርመን በአጠቃላይ ከግሪክ ወደ 900 የሚሆኑ ስደተኞችን አምጥታ በተለያዩ ግዛቶች ጥገኝነት ትሰጣለች። ጀርመን ያለባትን ኃላፊነት በዚህ መልኩ ትወጣለች ያሉት ዜሆፈር ፤ 12 የአዉሮጳ ሃገራት ስደተኞችን እንደሚቀበሉ ተናግረዋል። ይሁንና እስካሁን የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት ሜዲተራንያንን አቋርጠዉ ከመጡትና በግሪክ እና በጣልያን ብሎም ከማልታ ካሉት ስደተኞች መካከል ተቀብለዉ በሃገራቸዉ ጥገኝነት የሰጥዋቸዉ ስደተኞች ቁጥር 1600 ብቻ ነዉ።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ