የፕሬዝዳንት ትርምፕና ፕሬዝዳንት ፑቲን የአላስካ ስብሰብና፤የአውሮፓ ጩኸትና ማሳሰቢያ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 6 2017የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሶስት አመት ተኩል በላይ የዘለቀውን የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ላማስቆም ከሩሲያው አቻቸው ፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በሚቀጥለው አርብ አላስካ ላይ ተገናኝተው ለመወያየት ቀጠሮ መያዛቸው ከተሰማ ጀምሮ አውሮፓ ከራሱና ከአሚሪካ ጋር ጭምር በሰፈው እየመከረ ነው። ሩሲያ ቀደም ሲል የራሷን የሰላም ሀሳብ በፕሬዝዳንት ትራምፕ የሩሲያ ልዩ መልከተኛ በኩል እንዳሳወቀች የተሰማ ሲሆን፤ ይህም በዋናነት ዩክሬን ሩሲያ በያዘቻቸው ግዛቶች ላይ እውቅና እንድትሰጥ፣ በዩክሬን ማንም የውጭ ሀይል እንዳይገባና ገለልተኛ እንድትሆን የሚጠይቅ እንደሆነ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ እራሳቸው ከስምምነት ላይ ለመድረስየተወሰነ የመሬት ልውውጥ ወይም ስቶ መቀበል ሊኖር እንደሚችል አመላክተዋል፤ “ የመሬት መቀያየር ተካሄዷል። ሩሲያኖች ብዙ መሪትን ይዘዋል። የተወሰኑት ወደ ዩክሬን እንዲመለሱ እንናደርጋለን” በማለት የስብሰባቸውን አላማና ግብ ጠቁመዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለነስኪ ግን ለሩሲያ የሚስጥ አንድ ኢንች መሬት እንደማይኖርና በግዛታዊ እንድነታቸውና ሉዕላዊነታቸው እንደማያደራደሩ ነው ደጋግመው ሲናገሩ የተሰሙት።
ያውሮፓ መሪዎች ጭንቀትና ማሳሰቢያቸው
ስብሰባው በጦርነቱ ዋና ተሳታፊና ተጠቂም የሆነችው ዩክሬንና በተዘዋዋሪም ቢሆን ተሳታፊ የሆኑት ያውሮፓ አገሮች ባልተወከሉበት የሚካሄድ መሆኑ ለዩክሬንም ላውሮፓ ጥሩ ያልሆነ ስምምነት ላይ እንዳይደረስ ነው የአውሮፓ ዋና ስጋት።
ባለፈው ሳምንት መጨርሻ የጀርመን፤ ፈረንሳይ፤ ጣሊያን ብርታኒያና ሌሎች ሰባት ያውሮፓ መሪዎች በፊርማቸው፤ ትናንት የ27ቱ የህብረቱ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒትሮች በስብሰባ፤ ዛሬ ደግሞ የህብረቱ አባል አገሮች በመግለጫ፤ ፕሬዝዳንት ትራም የሩሲያን ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም የሚያደርጉትን ጥረት አውድሰው፤ መረጋጋትንና ደህንነትን ማረጋገጥ የሚችል ሰላም ግን የአገሮችን ነጻነት ሉላዊነትንና አለማቀፋዊ ህግን ማክበር ያለበት መውሆኑን አስገንዝበዋል።፡
በነገው እለትም የጀርመኑ ቻንስለር ፌሬሬሺክ ሜርዝ የአሜሪካራው ፕሬዝዳንት ዶላንድ ትራምፕና ፕሬዝዳት ዘለንስኪ የሚገኙበት የፈርንሳይ፣ ፊንላንድ፣ ጣሊያን፤ ፖላንድ፤ ብርታኒያና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ልዩ ስብሰብ መጥራታቸው ታውቋል። ቻንስለር ሜርዝ የጠሩት ስብሰባ በሩሲያ ላይ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ተጨማሪ ጫናዎች፣ በሩሲያ በተያዙት የዩክሬን ግዛቶች፣ የዩኪረን የድህንነት ዋስትና ጉዳይና በሰላም ውይይቱ ቅደም ተከተል ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ የቻንስለሩ ቃል አቀባይ አስታውቀዋል።
ይህ ሁሉ እሩጫና መዋከብ ዩክሬንና ያውሮፓ ህብረት ባልተወከሉበትና በሌሉበት የሚደርስብት ስምምነት ይልቁንም አፍራሽና ወደአንድ ወገን ያጋደለ እንዳይሆን በመስጋት እንደሆነ ይገምታል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቻንስለር ሜርዝ በጠሩት ስብሰባ ለመገኘት መወሰናቸው የዩክሬንን ጥያቄና ያውርፓንም ስጋት ከግምት ውስጥ ማስጋባታቸውን ያሳይል የሚሉ ወገኖች ፕረዝዳንቱ በቀጣይ ሰፊ ተሳትፎ ያለበት ውይይት ይጠሩ ይሆናል በማለት ተስፋ ግምታቸው ይገልጻሉ።፡
የሰሰባው ተጠባቂ ውጤት
በመሆኑም በዚህ ሁሉ ማሳሰቢያና ውትወታ መካከል በሚቀጥለው አርብ ፕሬዝዳንት ትራምፕና ፑቲን ተገናኝተው የሚያደርጉትን ውይይትና የሚደርሱበትን ስምምነት ከወዲሁ መናገር በርግጥ አስቸጋሪ ነው።
በለንደን ኮሌጅ የሩሲያ ፖሊሲ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ዶሚቲላ ሳግራሞሶም ግን በዚህ መካከልም ተሁኖ በተወሰኑ አጀንዳዎች ላይ ከምምነት ሊደረስ ይችላል ያላሉ፤ “ አንድ አይነት የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ ሊደረስ ይችላል፡ ሩሲያ የተቆጣጠርችው የዩክሬን መሬት ለግዜው በሩሲያ እንዲቆይ ስምምነት ላይ ሊደረስ ይችላል የሚል አስተያየትም አለ” በማለት የያዟቸውን መሬቶች መቀያየር የሚለው ሀሳብ ተግባራዊነት ግን እንደማይታቸው ተናግረዋል። በሌላ በኩል የአውሮፓ መሪዎችም ሆኑ ሚኒስትሮች በሳምንቱ ውስጥ በጋዛ እየደረሰ ስላለው እልቂትና እስራኤልም ጦርነትና ማፈናቀሉን ለመቀጠል መወሰኗን በሚመለክት ጠንካራ አቁም ያራምዳሉ ተብሎ ተጠብቆ የነበር ቢሆንም አውሮፓ ግን ለግዜው ትኩረቱና ጭንቀቱ የፕሬዝዳንት ትርምፕና ፕሬዝዳንት ፑቲን ያላስካ ስብሰባ ላይ ሆኖ ቀጥሏል።
ገበያው ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ