የፓሪስ ሳን ዠርማን እና የአርሰናል የሻምፕዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 29 2017ማስታወቂያ
በመላው ዓለም የእግር ኳስ አፍሪቃዎች ዘንድ ሲጠበቅ የቆየው የፓሪስ ሳን ዠርማን እና የአርሰናል እግር ኳስ ቡድኖች የአውሮጳ ሻምፕዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ፓሪስ ውስጥ ይካሄዳል። ትናንት በነበረው ተመሳሳይ የጣሊያኑ ኢንተር ሚላን የስፔኑ ባርሴሎናን አራት ለሦስት አሸንፎ ለፍፃሜ በቅቷል። የዛሬው ግጥሚያ አሸናፊ ከኢንተር ሚላን ጋር ለዋንጫ ይጫወታል።
የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታቀደም ሲል በነበረው ግጥሚያ ፓሪስ ሳን ዠርማ አርሰናልን አንድ ለዜሮ ማሸነፉ ይታወሳል። የዛሬውን ጨዋታ ለመከታተል የፓሪስዋ ዘገቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ጨዋታው በሚካሄድበት በፓሪሱ ፓርክ ደ ፕረንስ ስታድዮም ትገኛለች። በቀጥታ ስርጭታችን ቃለ መጠይቅ አድርገንላታል ።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ