የፍራንኮ ጀርመን ዲፕሎማሲ በአዲስ ምዕራፍ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 30 2017ማስታወቂያ
ፈረንሳይ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጠናቀቀበትን የውሮጳ የድል ቀን ዛሬ አስባ ዋለች። ከምርጫ በኋላ በመጀመሪያው የአውሮጳ ጉዟቸው ትናንት ረቡዕ ወደ ፓሪስ ያቀኑት የጀርመኑ መራሔ መንግስት ፍሬድሪክ ሜርስ አውሮጳ ትልቅ ስጋት እንደተደቀነባት ተናግረዋል።
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቅ 80ኛው ዓመት በሚዘከርበት ዕለት ወደ ፈረንሳይ የተጓዙት መራሔ መንግስት ሜርስ ፈታኙን ጊዜ ለማለፍ ፈረንሳይ እና ጀርመን ትብብራቸውን ማጠናከር የግድ የሚላቸው ጊዜ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል።
በጀርመን መራኄ መንግስት ፍሪድሪሽ ሜርስ ሹመት የታየው ድንጋጤና እፎይታ
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በበኩላቸው ፈረንሳይ እና ጀርመን አውሮጳን ከገጠማት ፈተና ለማውጣት በወታደራዊ እና ደህንነት ፣ በኤኮኖሚ እና በቴክኖሎጂ የምርምር ዘርፎች ትብብር በማጠናከር ከሃገራቱ ባሻገር አህጉራዊ አንድንቱን ለማጽናት መሰረት ነው ብለዋል። የሁለቱ ሃገራት መሪዎች መገናኘት ተቀዛቅዞ የቆየውን የሃገራቱን ግንኙነት በአዲስ ምዕራፍ ለማጽናት መደላድል ሳይሆናልቸው እንደማይቀር ተገምቷል።
ኃይማኖት ጥሩነህ
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ