የግዢው ብልጽግና ፓርቲ ዓምስት ዓመታት
ሰኞ፣ ኅዳር 23 2017ብልጽግና ፓርቲ ዕሴቶቼ በሚል ከዘረዘራቸው ጉዳዮች መካከል ሀገራዊ አንድነት፣ የዜጎች ክብር እና ነፃነት ይጠቀሳሉ። የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰሞኑን ባደረጉት ንግግር ብልጽግና ፓርቲ "የኢትዮጵያውያን ሁሉ የወል እውነት ነው" ብለዋል። አብዝተው ፓርቲያቸውን ያወደሱት ዐቢይ የደርጉን ገዢ ፓርቲ ኢሰፓን፣ የወቅቱን ብርቱ ተቃዋሚ ኢሕአፓን፣ ሕወሓትንና ኦነግን በኮሙኒስትነት ፈርጀው ችግራቸውንም ዘርዝረዋል። "ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች የተሻለ እሳቤ እና ሀሳብ ከማፍለቅ ይልቅ የተሻለ ሴራ መጎንጎን እንደ ብቃት የወሰዱ ስለሆኑ አላደጉም።የኦነግ አቤቱታና የብልጽግና ፓርቲ መልስ
ወቀሳ የቀረበበት ኢሕአፓ ግን መልሶ ብልጽግናን ተችቷል። የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሃይማኖት አብርሃም። "ሰላም ማጣቱ ለሰላማዊ ትግሉ እንቅፋት ሆኗል"።
የብልጽግና ብሬዝዳንት በፓርቲያቸው አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ንግግር ሲያደርጉ "በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት" የሚል ንግግር ሲያደርጉ ተደምጠዋል። ምንም እንኳን ፓርቲው ያሸነፈበት የሥልጣን ዘመን ከሁለት ዓመታት በታች የቀረው ቢሆንም። በቀጣይ እንሠራለን ካሏቸው ተግባራት መካከል "የኢትዮጵያ ሕልውና ጥያቄ ውስጥ የማይገባበት" ማድረግ ይጠቀሳል። የኢሕአፓው ምክትል ሊቀመንበር ግን "ምርጫ እየደረሰ ነው ግን ምንም ማድረግ እኛ ልቻልንም" ሲሉ ሁኔታው አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኦሮምያ ብልጽግና አመራሮች ጊዜያዊ እገዳ፤የኦነግ አመራሮች ውዝግብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፓርቲያቸው መድረክ ላይ ታጣቂዎች ምርጫቸው ወደ ሰላም መምጣት ብቻ መሆኑን አበክረው ገልፀዋል። "ፈተናዎቻችን በሪፎርም፣ በንግግር፣ በተሃድሶ ኮሚሽን ፣ በሽግግር ፍትሕ፣ ሰጥቶ በመቀበል መርህ፣ እየተፈቱ እንደሚሄዱ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉም ተደምጠዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ እና ፌዴራሊዝም መምህሩ ዶክተር ሲሳይ መንግሥቴ ስለ ሰላም የተደረገውን ጥሪ በዐወንታ የሚጠቀስ ቢሆንም አታሸንፉንም በሚለው ላይ ግን አስፈላጊነቱ ላይ ጥያቄ አላቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "ባልፉት ስድስት ዓመታት ከአንድም ጎረቤቶቻችን ጋር አንዲት ጥይት አልተቀያየርንም" ያሉት ንግግራቸውን በተመለከተም ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ የተከተለው የውጭ ግንኙነት መርህ በጎረቤት ሀገራት ትኩረት መስጠቱን በበጎ ጠቅሰው ግጭት የለም ማለት ግን ኢትዮጵያ በጎረቤቶቿ ለችግር አልተጋለጠችም ማለት እንዳልሆነ አስረድተዋል።
«ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የውህደት ውይይት አልጀመርኩም» ህወሓት
"እንዳለ መቅዳትን" አንዱ የፖለቲካ ድርጅቶች ችግር አድርገው የጠቀሱት የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ የፀጥታ ተቋማት ላይ ተደረገ ያሉት ለውጥንም አወድሰዋል። የፖለቲካ ተንታኙ እንደሚሉት ግን "የብሔር ፖለቲካ" የኢትዮጵያን የአስተዳደር ሂደት ቅርቃር ውስጥ ከትቶት እንደነበር ጠቅሰው አሁንም ቢሆን በየክልሉ የብሔር መልክ ያለው አደረጃጀት መኖሩን በአሉታ ጠቅሰዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ