የጀርመንና የአፍሪቃ ንግድ ማሽቆልቆል
ዓርብ፣ መስከረም 15 2013ማስታወቂያ
የጀርመንና የአፍሪቃ የንግድ ልዉዉጥ በተገባደደዉ የጎርጎሪያን 2020 ዓመት በእጅጉ ማሽቆልቆሉን ባለሐብቶችና ባለሙያዎች አስታወቁ። አምና ከጥር እስከ ሐምሌ በነበረዉ ሰባት ወር ከአፍሪቃ ወደ ጀርመን የገባዉ ሸቀጥ 10.4 ቢሊዮን ዩሮ የሚያወጣ ነዉ። በዚሁ ጊዜ ከጀርመን ወደ አፍሪቃ የተላከዉ ሸቀጥ ደግሞ የ11.6 ቢሊዮን ነዉ። የምጣኔ ሐብት አዋቂዎች እንደሚሉት አምና ከአፍሪቃ ወደ ጀርመን የገባዉ ሸቀጥ ብዛት ሐቻምና በተመሳሳይ ጊዜ ከገባዉ በ3.6 ቢሊዮን ዩሮ ሲቀንስ፣ ከጀርመን ወደ አፍሪቃ የተላከዉ ደግሞ በ2.6 ቢሊዮን ዩሮ አሽቆልቁሏል። ለንግድ ልዉዉጡ ማሽቆልቆል፣ የዶቼቨለዉ ዘጋቢ ዳኤል ፔልስ እንደሚለዉ የኮሮና ተሕዋሲ ወረርሺኝ ቀዳሚዉ፣የአፍሪቃ ሐገራት የፀጥታ ችግር ተከታዩ ምክንያቶች ናቸዉ።
ዳንኤል ፔልስ/ ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ