የቀኝ አክራሪዎች ሥጋት
ረቡዕ፣ መስከረም 23 2011ማስታወቂያ
ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ ምሥራቅ እና ምዕራብ ወይም ሶሻሊስት እና ካፒታሊስት በሚል ለአርባ አምስት ዓመታት ያክል ለሁለት ተገምሳ የነበረችዉ ጀርመን ዳግም የተዋኻደችበት 28ኛ ዓመት በዓል ዛሬ ተከብሯል። ዕለቱ በተለይ ርዕሠ-ከተማ በርሊን ዉስጥ በፀሎት፤ በፖለቲከኞች ንግግር እና ድግስ እየተከበረ ነዉ። የፖለቲካ መሪዎች እና የኃይማኖት አባቶች ዕለቱን አስመልክተዉ ባስተላለፉት መልዕክት እየተጠናከረ የመጣዉን የዘረኝነት አስተሳሰብን አጥብቀዉ አዉግዘዋል። በተለይ የጀርመን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ቮልፍጋንግ ሸወብለ ባስተላለፉት መልዕክት ቀኝ አክራሪዎች ሕዝቡን ከመከፋፈል እና ከማጋጨት እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ