የጀርመን ወግ አጥባቂ ፖለቲከኛ ፍሬድሪሽ ሜርስ መራሔ መንግስት ሆነዉ ተመረጡ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2017ማስታወቂያ
የጀርመን ወግ አጥባቂ የፖለቲካ ማሕበር የክርስቲያን ዴሞክራቶች ሕብረት (CDU) መሪ ፍሬድሪሽ ሜርስ ዛሬ የሐገሪቱ መራሔ መንግስት ሆነዉ ተመረጡ።የጀርመን ምክር ቤት (Bundestag) ሜርስን ለመራሔ መንግስትነት የመረጠዉ ለሁለተኛ ጊዜ በሰጠዉ ድምፅ ነዉ።ምክር ቤቱ ዛሬ ማርፈጃዉ ላይ ባደረገዉ ምርጫ ሜርስ ያገኙት 310 ድምፅ ለመራሔ መንግስትነት ለመመረጥ የሚያበቃቸዉ አልነበረም።በጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ታሪክ ለመራሔ መንግሥትነት የታጨ ፖለቲከኛ በመጀመሪያዉ ዙር ምርጫ ሳይመረጥ ሲቀር ሜርስ የመጀመሪያዉ ናቸዉ።በሁለተኛዉ ዙር ምርጫ ሜርስ ያገኙት ድምፅ 325 ነዉ።የፖለቲካና የሕግ ጉዳይ ተንታኝ ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ዛሬ ጀርመን ምክር ቤት የተከሰተዉን አዲስ ገጠመኝ «የፖለቲካ ቀዉስ» ብለዉታል።
ለማ ይፍራሸዋ / ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ሥለሺ