የጀርመን ኢምባሲ ለካንሰር ህሙማን የ50 ሺ ዩሮ ድጋፍ አደረገ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 25 2012ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ለካሰር ህሙማንን ነጻ የማደሪያ እና የምግብ ድጋፍ ለሚያደርግ በጎ አድራጎት ድርጅት የሀምሳ ሽህ ዩሮ እና የኮሮና መከላከያ ቁሳቁስ ረዳ። ኤምባሲው እርዳታውን የለገሰው የኮሮና ተኅዋሲ ያስከተለውን ጫና እንዲቋቋም ጎጆ ለተባለው የህሙማን ማረፊያ ማዕከል ሲሆን፤ የተለገሰው ገንዘብ የታማሚዎቹን የስድስት ወራት የምሳና እራት ወጪ ይሸፍናል ሲሉ የማዕከሉ መስራችና ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰላሜነሽ ፅጌ ገልፀዋል። በጀርመን ኢምባሲ የልማት ጉዳዮችና የሰብዓዊ ድጋፍ ፕሮጀክት ሃላፊ ማርከስ ቦክ ህሙማኑ ከኮሮና ወረርሽኝ ራሳቸውን እንዲጠብቁ መክረዋል።
ሶሎሞን ሙጨ
ፀሀይ ጫኔ
እሸቴ በቀለ