የጀርመኑ ቻንስለር ፍሪድሪሽ ሜርስ የአሜሪካ ጉብኝትና አንድምታዉ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 26 2017የጀርመኑ ቻንስለር ፍሪድሪሽ ሜርስ የአሜሪካ ጉብኝት እና አንድምታዉ
አዲሱ የጀርመን ቻንስለር ፍሪድሪሽ ሜርስ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለመገናኘት ሐሙስ ወደ ዋሽንግተን ይጓዛሉ። ባለፈዉ ቅዳሜ የጀርመን መራሔ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርስ የፊታችን ሐሙስ ለጉብኝት ወደ አሜሪካ እንደሚቀኑ የገለፁት የጀርመንና የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ናቸዉ። ሜርስ በነጬ ቤተመንግሥት ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ሲገናኙ ምን ይጠብቃቸዉ ይሆን?አዲሱ የዶናልድ ትራምፕ ቀረጥ እና የተቀረው ዓለም ምላሽ የጀርመኑ ቻንስለር ሜርስ በምርጫ ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ወደ አሜሪካ ለይፋዊ ጉብኝት ሲያቀኑ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑ ነዉ። ይህ ጉብኝት በአሜሪካ እና በአዉሮጳ አጋሮችዋ መካከል በንግድ ቀረጥ ጭማሪ ዉዝግብ ብሎም በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ባለዉ ግጭት ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት በተፈጠረበት ወቅት ነው። ከጀርመኑ ቻንስለር ከፍሪድሪሽ ሜርስ የአሜሪካ ጉብኝት ምን ይጠበቃል?ማሕደረ ዜና፣ የዩክሬን ጦርነት፣ የምዕራብ-ምሥራቆች ፍጥጫ አብነት
በሌላ በኩል የቀድሞዋ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ በኒውዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለጠቅላላ ጉባኤ መሪ ሆነዉ ተሾመዋል። ቤርቦክ በዚህ ቦታ ላይ ለመወዳደር የቀረቡ ብቸኛዋ እጩ መሆናቸው ታዉቋል። ከሁለት ሳምንት በፊት ቤርቦክ ቦታዉን ለመዉሰድ ባደረጉት የማመልከቻ ንግግር፣ «በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ እና በሌሎች ሀገራት ከሚታየዉ የማግለል ዝንባሌ አንፃር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከምንጊዜውም በላይ በአሁኑ ወቅት አስፈላጊ ነዉ» ሲሉ ተናግረዉ ነበር።ለአዲሱ የዶናልድ ትራምፕ ቀረጥ የአውሮጳ ህብረት ምላሽ ምን ይሆን ?
የቀድሞዋ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒ ስትር አናሌና ቤርቦክ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚደንትነት በምዕራብ አውሮጳ አገሮች እና በሌሎች የዓለም ሃገራት ይደገፋል። አዲሷ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት አናሌና ቤርቦክ የስልጣን ዘመናቸው የሚጀምረው ከፊታችን መስከረም ወር ይሆናል። ስልጣኑም ለቀጣይ አንድ ዓመት የሚዘልቅ ነዉ። የቀድሞዋ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ በኒውዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለጠቅላላ ጉባኤ መሪ ሆነዉ መሾማቸዉ አንደምታዉ ምንድን ነዉ? በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል። የድምፅ ማድመቻ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።
አበበ ፈለቀ / አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ