ፖለቲካሰሜን አሜሪካ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የመካከለኛዉ ምሥራቅ ጉብኝት
ማክሰኞ፣ ግንቦት 5 2017ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሶስት የፋርስ ባህረ-ሠላጤ አካባቢ ሐገራትን ለመጎብኘት ዛሬ ሪያድ ሳዑዲ አረቢያ ገብተዋል።ትራምፕ ከሳዑዲ አረቢያ በተጨማሪ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችንና ቀጠርን ይጎበኛሉ።የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ዛሬ ሪያድ ሲገቡ ልዩ አቀባባል ተደርጎላቸዋል።ቀጠር ደግሞ «የሠማይ ላይ ቤተ-መንግሥት» የተባለ ልዩ አዉሮፕላን ለትራምፕ ሠጥታለች።የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ባሁኑ ጉዟቸዉ የአሜሪካ ጥብቅ ወዳጅ እስራኤልን ለመጎብኘት አለማቀዳቸዉ እያነጋገረ ነዉ።ትራምፕ ሶስቱን የአረብ ሐገራት የሚጎበኙት የጋዛዉ ጦርነት አሰቃቂ እልቂት ማስከተሉ በሚዘገብበት፣ ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን በሚደራደሩበት ወቅት ነዉ።
አበበ ፈለቀን
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ