የዘር ጥላቻ በጀርመን
ማክሰኞ፣ ሰኔ 9 2012ማስታወቂያ
ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ በሐገሩ ፖሊስ በአሰቃቂ ግፍ ከተገደለ ወዲሕ የዘር ጥላቻን በመቃወም በመላዉ ዓለም የተቀሰቀሰዉ ሕዝባዊ ንቅናቄ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።የሕዝቡ ሰልፍና ዉግዘት መንግሥታት፣ ፖለቲከኞች፣ ሙሕራንና መገናኛ ዘዴዎች በየሐገራቸዉ በሚኖሩ ጥቁሮች፣ክልሶችና የዉጪ ተወላጆች ላይ የሚደርሰዉን ግፍና በደል እንዲያጤኑና እንዲያጋልጡ እያስገደዳቸዉ ነዉ።ጀርመን ዉስጥ ነጭ ባልሆኑ ዝርያዎች፤ በአናሳ ሐይማኖት ተከታዮችና ለየት ያለ የፆታ ዝንባሌ ባላቸዉ ሰዎች ላይ ከፍተኛ በደል እንደሚፈፀም ጥናቶች አረጋግጠዋል።የዛሬዉ አዉሮጳና ጀርመን ዝግጅታችን ጀርመን ዉስጥ የሚታየዉን የዘር ጥላቻና መፍትሔዉን የሚጠቁም ዘገባ ይቀርብበታል።ራልፍ ቦዘን ያጠናቀረዉን ዘገባ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ተርጉሞታል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ