ማስታወቂያ
ድንበር የለሽ የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ኢትዮጵያ በዓለም የፕሬስ ነጻነት መመዘኛ ደረጃዋ ዘንድሮም ማሽቆልቆሉን ይፋ አደረገ ። ኢትዮጵያ በጎርጎሪዮሱ 2024 ዓመት ከነበረችበት የ141ኛ ደረጃ በአራት ማሽቆልቆሏ ተገልጧል ። ኤርትራ በድርጅቱ መዘርዝር ውስጥ ከሠፈሩ 180 የዓለም አገራት ዘንድሮም የመጨረሺያው ደረጃ ላይ ትገኛለች ።
በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሱዳን ጦር ሠራዊት አባላት በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ገለጡ ። ዋና ከተማዪቱ ካርቱምን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን በማባረር የተቆጣጠሩት የሱዳን ጦር ኃይል ታጣቂዎች ኢትዮጵያውያኑ ላይ የበቀል የሚመስል ርምጃ እየወሰዱ እንደሆነም ስደተኞቹ ተናግረዋል ።
በጀርመን የደኅንነት መሥሪያ ቤት በዐይነ ቁራኛ ክትትል ሲደረግበት የቆየው መጤ ጠሉ አማራጭ ለጀርመ ፓርቲ (AFD)ዛሬ በቀኝ አክራሪነት ተፈረጀ ። ፓርቲው የተላለፈበትን ፍረጃ በተመለከተ በፍርድ ቤት አቤቱታ ለማሰማት መወሰኑ ታውቋል ።