የዋጋ ውድነት የተጫነው የበዓል ገበያ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 12 2014በብሔራዊ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ ጥናቶችና የኢኮኖሚክ ቆጠራዎች ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አማረ ለገሰ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ማብራሪያ የዋጋ ንረቱ ያለፉትን 2 ወራት ውጤት እንኳ ሲታይ የዋጋ ጭማሪው አጠቃላ ሁኔታ የ34 በመቶ ማሻቀብ ሲያሳይ በምግብ ላይ እስከ 43 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ተስተውሏል፡፡
መጪው የሳምንቱ መጨረሻ የትንሳኤ በዓል እና ከአንድ ሳምንት በኋላ የሚከበረውን የኢድ በዓል መዳረሻ ላይ በደረስንበት ባሁን ዋጋ ዋጋው እንደማይቀመስ ሸማቾችም አምርረው ይገልጹታል፡፡
በአዲስ አበባ ኮልፌ ክፍለ ከተማ ጦር ኃይሎች አደባባይ ተብሎ በሚታወቀው ስፍራ በንግድ ትርዒት ላይ የራሷ ምርት የሆነውን እንቁላል ይዛ በመቅረብ አንዱን በሰባት ብር የምትሸጠው ወጣት ሰናይት ግን አምራቾችን ከሸማቾች ቀጥታ ማገናኘቱ ጥሩ መፍትሄ መሆኑን እኛ ማሳያ ነን ትላለች፡፡ አፕ…
ገቢያውን ያረጋጋሉ በሚል እምነት ከወጡትና ለበዓል መዳረሻ የሚሆን የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች ከያዙት ሌሎችንም አነጋግረናል፡፡
ሌላው አሁን ያለውን የሸማቾች ፍላጎት ያረጋጋሉ ተብለው በአሁን ወቅት ወደ ገቢያው ከተሰማሩት የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ይጠቀሳሉ፡፡ አቶ ታምሩ አባገሮ ቤዛ ሸማቾች ህብረት ስራ ማህበርን በዋና ስራ አስኪያጅነት የሚመሩ ናቸው፡፡ ሸማቾች ግን ይጠይቃሉ፡፡ ይህም ርካሽ አሊያም ተመጣጣጨኝ ዋጋ ሊባል የሚችል አይነት አይደለም፡፡
የቤዛ ሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር ኃላፊ አቶ ታምሩ ግን የዋጋ ንረቱ ሌሎች ምክኒያቶችም ያለው ነው ባይ ናቸው፡፡
የዋጋ ንረት መስተዋል ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴው መልካም ቢሆንም በአንድ ዲጂት ብቻ መገደብ ያለበት ነው የሚሉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግት የስታቲስቲክስ ጥናቶችና የኢኮኖሚክ ቆጠራዎች ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አማረ ለገሰ ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት ፈታኝ ሲሉም በመግለጽ መፍትሄንም ጠቃቅሰዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ