የኮቪድ 19 ክትባት በጀርመን
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 19 2013ማስታወቂያ
የአውሮጳ ሕብረት አባል ሃገራት የኮቪድ 19 ተሐዋሲ መከላከያ ክትባት በትናንትናው ዕለት መስጠት ጀምረዋል። ለጊዜው የተጀመረው እያንዳንዱ የሕብረቱ አባል ሀገር በሚያስፈልገው መጠን ሳይሆን በክፍተኛ መጠን ተጋላጭ ለሆኑት እንዲዳደረስ በሚል ከ10 ሺህ ያልበለጠ ክትባት መከፋፈሉም ተነግሯል። ጀርመን ውስጥ ትናንት ክትባቱ መሰጠት የተጀመረው በአዛውንት መጦሪያ ማዕከላት በሚገኙ አረጋውያን ነው። ክትባቱ ከተጀመረባቸው የአዛውንት መጦሪያ ማዕከላት በአንዱ 70 የሚሆኑ ነዋሪዎች ቢገኙም ለመከተብ ፈቃደኛ የሆኑት 12ቱ ብቻ ናቸው። የኮቪድ 19 ክትባት ትናንት መሰጠት ተጀምሯል፤ እስካሁን በዕድሜ የገፉና በአዛውንት መጦሪያ ማዕከላት የሚገኙት መከተባቸው እየተነገረ ነው። በርሊንና አካባቢው ተሐዋሲው ከተስፋፋባቸው መካከል ይጠቀሳሉ፤ የእንቅስቃሴ ገደብ ሲጣልም ቀደም ብሎ ነውና የኅብረተሰቡ ስሜት እንዴት ነው? ስል በርሊን የሚገኘው ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ጠይቄዋለሁ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ