የኮሮና ሥጋት በኢትዮጵያ የሥደተኛ መጠለያ ጣብያዎች
ዓርብ፣ መጋቢት 25 2012ማስታወቂያ
የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣብያዎች ከፍተኛ አደጋ የተደቀነ ነዉ ተባለ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በኢትዮጵያ በሚገኙ የስደተኛ መጠልያ ጣብያዎች ውስጥ የሚኖሩ ኤርትራውያንና ሶማልያውያን ስደተኞች የኮረና ቫይረስ ወረርሺኝ ስጋት እንዳለባቸው ይናገራሉ፡፡ በኮምፖቹ የሚገኙ ስደተኞች እንደሚሉት በመጠልያዎቹ ያለው የውሃ እጥረት፣ የፅዳት መጠበቅ ቁሳቁስ ውሱንነት፣ የሕክምና ዝግጁነት ጉድለት እንዲሁም ሌሎች ችግሮች ስደተኞቹን ያስጨነቀ ሆንዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ በበኩሉ በኢትዮጵያ በሚገኙ 28 የስደተኛ መጠልያ ጣብያዎች ውስጥ የቫይረሱ ወረርሺኝ እንዳይከሰት የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየከወነ መሆኑ ይገልፃል።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ