የእስራኤል እና የሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት
ሐሙስ፣ ጥር 8 2017
ስራኤልና ሃማስ አስራ አምስት ወራት የዘለቀውን ጦርነት በማቆም ታጎቾችንና እስረኖችን ለማስለቀቅና ለማስፈታት፤ የሰባዊ እርድታ እንዲገባ ለማድረግና ለዘላቂ ሰላም በጋራ ለመስራት ትናንት ዶሃ ካታር ላይ የተስማሙ መሆኑ ተገልጿል። በአሜሪካ ቃታርና ግብጽ አደራዳሪነት ከስምምነት የተደርሰበት የሁለቱ ወገኖች ስምምነት፤ ሶስት ምዕራፎች ያሉትና ከሚቀጥለው ዕሁድ ጀምሮ የሚተገበር መሆኑ ተግልጿል።፡
ድርድሩን የመሩት የቃታር ጠቃላይ ሚኒስተር ሺክ ሞሃመድ ቢን አብዱርሁማን ቢን ጃሲም አል ታኒ አደራዳርዎቹን ወክለው ትናንት በሰጡት መግለጫ፤ ሁለቱ ወገኖች ታጋቾችን ለመልቀቅና እስረኖችን ለመፍታት የሰባዊ እርድታም እንዲገባ ለማድረግ የተስማሙ መሆኑን አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ባይደን በበኩላቸው ድርድሩ ቀላል እንዳልነበር አስታውሰው መንግስታቸው ከዚህ ስምምነት እኒዲረስ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን ገልጸዋል፤ “ ይህን ጦርነት ለማስቆም ከዚህ የተሻለ ስምምነት አልነበረም። በተለይ ለታጋች ቤተሰቦችና በጦርነቱ በእጅጉ ለተጎዱት ፍልስጤሞች ይህ ቀን ትልቅ ቀን ነው” በማለት በወጤቱ የተደሰቱ መሆኑን አስታውቀዋል።
የጦርነቱ ጅማሮና ያስከተለው ጉዳት
በአሜሪካ የአውሮፓ ህብረትና እስራኤል በአሸባሬንት የተፍፈረጀው ሃማስ መክሰረም 26 2016 አም በሰላማዊ የእስራኤል ዘጎች ላይ ጥቃት በመፈጸም 1200 ሰዎችን ገድሎ፤ 250 ሰዎችን አግቶ መውሰዱን ተከትሎ፤ እስራኤል እሳክሁንም ድረስ በተለይ በጋዛ እያደሰረች ባለው ጥቃት ከ46 ሺ በላይ ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉና ሁለት ሚዮን የሚሆኑ እንደተፈናቀሉ ከጋዛ መስተዳድርና አለማቀፍ ድርጅቶች የወጡ መርጀዎች ይፋ አድርገዋል።
በስምምነቱ የአለም መሪዎች አስተያየት
ጦርነቱ እንዲቆምና ታጋቾች እንዲለቁቁ በጋዛ የፍልስጤሞች ግድያና መፈናቀል እንዲቆም ከየአቅጣጫው ጥሪ ሲደረግ የቆየ ቢሆንም፤ በተለይ እስራኤል ጆሮ ዳብ ልበስ ብላ ነበር የቆየችው። ትናንት ይህ ስምምነት ተደረገ ሲባል ግን አለም ሁሉ ደስታውን ሲገልጽና ስምምነቱ እንዲጸናና ተግብራዊ እንዲሆን መልክቱን ሲያስተላልፍ ነው የተሰማውና የታየው ። የመንግስትቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴረሽ ባስተላለፉት መልክትም፤ “ታጋቾችን የሚያስለቅቅና እስረኖችን የሚያስፈታ የተኩስ ማቆም ስምምነት መደረጉ ይበል የሚያሰኝ ነው” በማለት ሁለቱ ወገኖች ከዚህ ስምምነት እንዲደርሱ ጥረት ያደረጉትን አደራዳሪዎች አመስግነው ሁሉም ግን ለስምምነቱ ተግባራዊነትና ተፈጻሚነት የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታቱ ሁለቱ ወገኖች የደረሱበትን የሰላም ስምምነትተገቢ፤ አንዳንዶች ደግሞ የዘገየ በማለት ግን ሁሉም ድጋፋቸውን ገልጸዋል። የህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ዞቮንዴርል ሌየን በቀድሞው ቲውተር በአሁኑ ኤክስ ገጻቸው ባስተላለፉት መልክት የተኩስ ማቆም ስምምነት መድረጉ፤ ታጋቾችና እስረኖች ከቤተሰቦቻቸው እንዲገናኙ የሚያደርግና የሰባዊ እርዳታ እንዲደርስ፤ ለዘላቂ ሰላምም በር የሜክፍት ጥሩ ጅማሮ መሆኑን ገልጸዋል።፡የጀርመን፤ ስፔን ቤልጅየም፤ አይርላንድ፤ ብራታኒይና ሌሎችቹም መሪዎች ስምምነቱ በመካከለኛው ምስራቅ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እንደሚረዳ ያላቸውን እምነት በመግለጽ ተግባራዊ እንዲሆን ጠይቀዋል።
ለሰላም ስምምነቱ መዘግየት የሚነሱ ትችቶችና የተመራጩ ፕሬዝደንት አስተያየት
ይህን መሰሉን ስምምነት ቀደም ብሎ በማረድግ የደረሰውን ሞትና ችግር ቢያንስ መቀነስ ይቻል ነበር የሚሉ ወገኖች፤ ለሰላም ስምምነቱ መዘግየት እስራኤልን ብቻ ሳይሆን እስከመጨረሻው ድጋፍ ስታደርግላት የቆየችውን አሜርካንም ተጠያቂ ያደርጋሉ። ፕሬዝዳንት ባይደድን ግን መንግስታቸው እስራኤልን እየረዳም ቢሆን ሰላም እንዲሰፍን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንና የዛሬው የሰላም ስምምነትም ባለፈው ግንቦት ወር መንግስታቸው ያቀረበው የሰላም ሀሳብና ከዚያ ወዲህ የተደረገውየዲሎማሲ ስራ ውጤት መሆኑን በማስታወስ፤ “ ከዚህ የሰላም ስምምነት የተደረስው በቀላሉ አይደለም። በውጭ ግንኑነት በሰራሁባቸው በርካታ አመታት ይህ አስቸጋሪውና ድርድር ነበር” በማለት በውጤቱ የረኩ መሆኑን አስታውቀዋል።
የፊታችን ሰኞ የአሜሪካንን በትረ ስልጣን የሚረከቡት ዶንልድ ትራምፕ በበኩላቸው ይህ ስምምነት የእሳቸው መመረጥና ወደ ስልጣን ዳግም መምጣት ውጤት መሆኑን በማህበራዊ ገጻቸው ጽፈው አስነብበዋል። ‘ገና ወደ ቤተመንግስት ሳንገባ ያስመዘገበው ድል ነው” በማለትም አሜሪካና አለምም ጭምር ወደፊት ከመግስታቸው ሌሎች ጥሩ ነገሮችን እንዲጠብቁም አሳስበዋል።
ገበያው ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ፀሀይ ጫኔ