የኤርዶኻን ጉብኝት ፤ የሜርክል ሥልጣን
ዓርብ፣ መስከረም 18 2011ማስታወቂያ
ጀርመንን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የቱርክ ፕሬዝደንት ሬሴፕ ጠይብ ኤርዶኻን ዛሬ በርሊን ቤተ-መንግሥት ሲደርሱ ደማቅ ወታደራዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።ኤርዶኻን ጀርመንን መጎብኘታቸዉ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ2016 በአመራራቸዉ ላይ የተቃጣዉ መፈንቅለ መንግስት ከከሸፈ ወዲሕ የሻከረዉ የሁለቱ ሐገራት ግንኙነት መሻሻሉን ጠቋሚ ነዉ።ይሁንና ፕሬዝደንት ኤርዶኻን ከጀርመንዋ መራሒተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር ያደረጉት ዉይይት ሁለቱ መንግስታት አሁንም ብዙ ልዩነት እንዳላቸዉ አመልክቷል።ሜርክል የቱርኩን መሪ ያነጋገሩት አመራራቸዉ ክፉኛ በተዳከመበት ወቅት ነዉ።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ