የኢትዮጵያ ፖሊስ የአዲስ ስታንዳድርን መረጃ ወይም ዳታ «እወስዳለሁ» አለ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 15 2017ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ባለፈዉ ሳምንት ከአዲስ ስታንዳርድ ቢሮና ባልደረቦች የወሰደዉን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ዛሬም አለመመለሱን የመገናኛ ዘዴዉ አዘጋጆጅና መስራች አስታወቁ።የፌደራል ፖሊስ ባልደረቦች ናቸዉ የተባሉ ሰዎች የታዋቂዉን ኢትዮጵያየግል የእንግሊዝኛ መገናኛ ዘዴን ቢሮ በርብረዉ ጋዜጠኞቹ የሚጠቀሙባቸዉን የድርጅቱን ኮምፒዉተሮች፣ የጋዜጠኞቹን ተንቀሳቃሽ ሥልኮችና ሌሎች ንብረቶችን ወስደዋል።የአዲስ ስታንዳርድ ዋና አዘጋጅ ዮናስ ከዲር እንዳለዉ ሲቢል የለበሱት ሰዎች ቢሮዉን ከመመዝበራቸዉ በፊት የድርጅቱን የIT ሠራተኛ መኖሪያ ቤት በሌሊት ወርረዉ የግለሰቡንና የባለቤቱን ተንቀሳቃሽ ስልኮች ወስደዋል።
ዐቢይ አህመድ ዓሊየኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የአዲስ ስታንዳደርድ ቢሮን መመዝበሩ አልበቃ ብሎ በወሰዳቸዉ ኮምፒዉተሮችና ሞባይሎች ዉስጥ የሚገኙ መረጃዎችን ለመዉሰድ መዛቱን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) አጥብቆ ተቃዉሞታል።የአዲስ ስታንዳርድ መሥራች ወይዘሮ ፀዳለ ለማ በበኩሏ የፖለስን ርምጃና ዛቻ «መንግሥት የመናገር ነፃነትን ከማፈን አልፎ ለመቆጣጠር» ማለሙን ያመለክታል ትላለች።
ቃለ መጠይቆቹን ለማድመጥ ከታች ያሉትን ማገናኛዎች ይጫኑ
ነጋሽ መሐመድ
ታምራት ዲንሳ