የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሪዎች በመቐለ ከትግራይ መሪዎች ጋር ተወያዩ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 10 2017
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እና ሌሎች ልኡካን በፌደራሉ መንግስት እና ህወሓት መካከል በተፈጠረው ውጥረት ላይ ዛሬ በመቐለ ከትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ባለስልጣናት፣ የህወሓት መሪዎች እና በክልሉ ከሚገኙ የሃይማኖት አባቶችና ሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ። በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ፕሬዝደንት ሼክ ሓጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው ልኡክ ከትግራይ ክልልግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እና ከክልሉ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር በዝግ ተወያይተዋል።
በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህወሓት መካከል ያለው ልዩነት በሰፋበት እና የግጭት ስጋት ባጠላበት በዚህ ወቅት ችግሩን ለመፍታት ያለመ ውይይት መደረጉን በሀገር ሽማግሌዎቹ እናየትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደርውይይት ከተሳተፉ ምንጮች ተረድተናል።
ይህ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ፕሬዝደንት ሼክ ሓጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው ልኡክ ይሁን በትግራይ በኩል በውይይቱ የተሳተፉ አካላት ይፋዊ መግለጫ ለመገናኛ ብዙሐን ከመስጠት ተቆጥበዋል። ከዛሬ ከሰዓት በፊት እና ከሰዓት በኃላ የተደረጉ ውይይቶች ለመገናኛ ብዙሐን ዝግ ነበሩ። በዚህ ላይ የመቀሌውን ዘጋቢያችንን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴን በስልክ አነጋግረነዋል።
ሙሉውን ቃለ መጠየቅ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያዳምጡ
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ / ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ